Wednesday, December 26, 2012

“ዘይሁብ መርሐ ርቱዓ ለቤተክርስቲያን”         በጸሎተ ኪዳን ዘሠርክ ላይ እንደተነገረው፥ ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ ለምትሆን፥ ጸጋን ኃይልን ለምታድል፥ አምነው ለሚቀርቡት ምስጋና አንድም በሃይማኖት ለሚገኝ ክብር ማረፊያ ማሳረፊያ ላደረጋት ለቤተክርስቲያን ቅን መሪ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። የተገረፈላት፥ሥጋውን የቆረሰላት፥ ደሙን ያፈሰሰላት፦ ነፍሱንም አሣልፎ የሰጠላት እርሱ ነውና። የሐዋ ፳፥፳፰።                                              
          ጥንት ሙሴን እና አሮንን ልጆቹንም ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የመረጠ እግዚአብሔር ነው። ዘጸ ፫፥፩-፳፪፣ ፳፰፥፩-፲፬ ። ይህንን ምርጫ ለመቃወም ወይም በምርጫው ጣልቃ ለመግባት የሞከሩ ዳታን፥ ቆሬንና አቤሮን ፍጻሜያቸው አላማረም። “እናንተ የሌዊ ልጆች ስሙኝ፤ የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማኅበር ለይቶ የመረጣችሁን የእግዚአብሔርን ድንኳን አገልግሎት ትሠሩ ዘንድ እንድታገለግሏቸውም በማኅበሩ ፊት ትቆሙ ዘንድ ወደ እርሱ ያቀረባችሁን ታሳንሱ ታላችሁን?” ብሎ የመከራቸውን ሙሴን አልሰሙትምና ዘኁ ፲፮፥፩-፶። ከቤተ መንግስቱም ሰዎች እነ ዖዝያን እግዚአብሔር የመረጣቸውን ገፍተው ቤተ መቅደሱን ደፍረው ነበር። “ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ታበየ፥ አምላኩንም እግዚአብሔርን በደለ፥ በዕጣን መሠዊያውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅደስ ገባ ካህኑም ዓዛርያስ ከእርሱም ጋር ጽኑዓን የነበሩ ሰማንያ የእግዚአብሔር ካህናት ተከትለው ገቡ። ንጉሡንም ዖዝያንን እየተቃወሙ፥ ዖዝያን ሆይ፥ ዕጣን ማጠን ለተቀደሱት ለአሮን ልጆች ለካህናቱ ነው እንጂ ለእግዚአብሔር ታጥን ዘንድ አይገባህም፥ ከእግዚአብሔር ርቀሃልና ከመቅደሱ ውጣ፥ ይህ በአም ላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ክብር አይሆንህም፥አሉት፤” ይላል። የንጉሡም መጨረሻ አላማረም። ፪ኛ ዜና ፳፮፥፲፮-፳፫                
                      
          እግዚአብሔር እርሱ ራሱ የመረጣችውንም ቢሆን የሚቀጣበት ጊዜ አለ። “የቅርብ ጠበል ልጥ ያርሱበታል፤ ዝቋላ የቅርቡ ያርሰዋል፥ የሩቁ ይሳለመዋል።’’ እንዲል፥ ቤተ እግዚአብሔርን  ደፍሮ ማስደፈር በቀረቡት የሚብስበት ጊዜ አለና ነው። የሊቀ ካህናቱ የአሮን ልጆች ናዳብና አብድዩ እግዚአብሔር ባላዘዛቸው እሳት፥ የእምነቱ ሥርዓት በማይፈቅደው መን ገድ የዕጣን መሥዋዕት በማቅረባቸው በሞት ተቀጥተዋል። ‘’እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥቶ በላቸው፤ (አቃጠላቸው)፤ በእግዚአብሔርም ፊት ሞቱ” ይላል። ዘሌ ፲፥፩-፪ ። ሙሴና አሮንም በሕዝቡ ገልበጥባጣነት እጅግ የተቆጡበት ጊዜ ስለነ በረ፥ “ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና፥ስለዚህ ወደሰጠኋችሁ ምድር ይህን ማኅበር ይዛች ሁ አትገቡም።” ተብለዋል። የእግዚአብሔር ቃል ነውና ከነዓን አልገቡም። ዘሌ ፲፥፩-፲፫ የሊቀ ካህናቱ የዔሊ ልጆችም በቅድ ስናው ሥፍራ ርኵሰትን ይፈጽሙ ነበር። አባታቸው  ‘’ሰውስ ሰውን ቢበድል ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩለታል፥ ሰው እግዚአ ብሔርን ቢበድል ስለ እርሱ ወደ ማን ይጸልዩለታል?’’ ቢላቸውም አልሰሙትም። ‘’እነርሱ ግን እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ወድዶአልና የአባታቸውን ቃል አልሰሙም። ‘’ ይላል። እግዚአብሔርም፥ ‘’ያከበሩኝን አከብራለሁ፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም። እነሆ፥ ዘርህንም የአባትንም ቤት ዘር የማጠፋበት ዘመን ይመጣል፤ በቤትህም ለዘላለም ሽማግሌ አይገኝም። በዓይኖቹ የሚፈጽም በነፍሱም የሚተጋ ሰውን ከመሠዊያዬ አላጠፋም። ከቤትህ የሚቀሩት ሰዎች ሁሉ ግን በጎልማሶች ሰይፍ ይሞታሉ።‘’ ብሎ ተናገረ። ፩ኛ ሳሙኤል ፪፥፳፪-፴፮ የተናገረውም ጊዜውን ጠብቆ በልጆቹ ላይ ተፈጸመ። ዔሊም “በመሥዋዕቴ ላይና በዕጣኔ ላይ ስለምን በክፉ ዓይን ተመለከትህ? የእስራኤል ልጆች በፊቴ  ከሚያቀርቡት መሥዋዕት ሁሉ በቀዳማያቱ ስለ አከበርኩህ ከእኔ ይልቅ ልጆችህን ለምን መረጥህ?” ተብሎ ነበርና የልጆቹን መርዶ እንዲሁም የታቦተ ጽዮንን በአሕዛብ እጅ መማረክ ሰምቶ፥ ከወንበሩ ወድቆ፥ አንገቱ ተቆልምሞ አጉል ሞት ሞቷል። እናታቸውም ይህንኑ ሰምታ በወሊ ድ ላይ ሞታለች። ፪ኛ ሳሙ ፪፥ ፳፱፣ ፬፥፩ በአዲስ ኪዳንም አገልጋዮችን ይመርጥ የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ‘’አሥራ ሁሉቱን ደቀመዛሙርቱን ጠርቶ ያወጡአቸው ዘንድ፥ በርኵሳን  መናፍስት ላይ ሥልጣንን ሰጣቸው።‘’ ይላል። የሐዋ ፲፥፩። ከዓለም ለይቶ የመረጣቸውን እነዚህን ‘’እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ የመረጣችሁኝ አይደለም፤ እንድትሄዱ ፍሬም እንድ ታፈሩ፥ ፍሬአችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ። እርስ በእርሳችሁም እንድትዋደዱ ይህን አዝዣችኋለሁ‘’ ብሎአችኋል። ዮሐ  ፲፭፥፲፮። ቅዱሳን ሐዋርያት የተከተሉት ይኽንኑ መንገድ ነው። “እንግዲህ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል፤’’ አሉ። ኢዮስጦስ የሚሉትን በርናባስ የተባለውን ዮሴፍን እና ማትያስን ሁለቱን ሰዎች አቆሙ፥ እንዲህም ብለው ጸለዩ፥ “አቤቱ ልብን ሁሉ የምታውቅ አንተ፥ ከእነዚህ ከሁለቱ የመረ ጥኸውን አንዱን ግለጥ። ይሁዳ ወደ  ገዛ ሀገሩ ይሄድ ዘንድ የተዋትን ይህቺን የአገልግሎትና የሐዋርያነትን ቦታ የሚቀበላትን ግለጥ፤” አሉ። ዕጣም አጣጣሏቸው፥ ዕጣውም በማትያስ ላይ ወጣ፥ ከአሥራ አንዱ ሐዋርያትም ጋር ተቆጠረ፥” ይላል። ማትያስን በዕጣ የመረጠ እግዚአብሔር ነው። ምክንያቱም ቅዱሳን ሐዋርያት ዕጣ ያጣጣሏቸው እግዚአብሔር እንዲመርጥ ነውና። የሐዋ ፩፥፳፪-፳፮። “በአንጾኪያ በነበረችው ቤተክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር የተባ ለው ስምዖን፥ የቄሬናው ሉቅዮስ፥ ከአራተኛው ክፍል ገዢ ከሄሮድስ ጋር ያደረው ምናሔ፥ ሳውልም ነበሩ። የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ፥ ሲጾሙም መንፈስ ቅዱስ፥ በርናባስን እና ሳውልን እኔ ለፈለግኋችሁ ሥራ ለዩልኝ አላቸው። ያን ጊዜም ከጾ ሙና ከጸለዩ፥ እጃቸውን በራሳቸው ላይ ከጫኑባቸው በኋላ ላኩአቸው።” የሚልም አለ። የሐዋ ፲፫፥፩-፲፫። ሲሞን መሠሪ ይህችን የእግዚአብሔር ምርጫ የሆነች ሥልጣን እንደ ሸቀጥ ለመሸመት ሞክሮ አልተሳካለትም። ቅዱስ ጴጥሮስ፥ “የእግዚ አብሔርን ጸጋ በገንዘብ ልትገዛ አስበሃልና ገንዘብህ ከአንተ ጋር ይጥፋ። በዚህ ነገር ዕድልና ርስት የለህም፥ በእግዚአብሔር ፊት ልብህ የቀና አይደለምና። አሁንም ከክፋትህ ተመለስና ንስሐ ግባ፥ የልቡናህንም  ሃሳብ ይተውልህ እንደሆነ እግዚአ ብሔርን  ለምን፤ በመራራ መርዝ ተመርዘህ፥ በዓመፃ ማሰሪያ ተተብትበህ አይሃለሁና።” ብሎታል። የሐዋ ፰ ፥ ፲፭ – ፳፬። በመጨረሻም በምትሐት ዐርጋለሁ ብሎ በሞከረ ጊዜ፥ ቅዱስ ጴጥሮስ ቢያማትብበት ወድቆ ተንቀጫቅጮ ሞቷል።                       
          እንግዲህ አባቶችም ልጆችም የምናውቀውና የምናምነው እውነት ይኽንን ቢሆንም፥ በቤተክርስቲያናችን የሚታ የውና የሚሰማው ሁሉ ግን ከዚህ እውነት እየራቀ ለመምጣቱ ምስክር መጥቀስ አያሻም። መንግስታት በተለዋወጡ ቁጥር በተፅዕኖ ቀኖና ቤተክርስቲያን እየፈረሰ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ፀሐይ የሞቀውን እውነት መሸፈን አይቻልም። የቤተክርስቲያንን መሪዎች የሚመርጠው እግዚአብሔር መሆኑ ቀርቶ ሌላ ኃይል ከሆነ ሊቀ ካህናቱ ዔሊ እንዳደረገው እግዚ አብሔርን ማሳነስ ነው። እንደ ንጉሡ ዖዝያን እግዚአብሔርን መድፈር ነው። ከእግዚአብሔር ቤት ተቀምጦ ከእንደዚህ አይነቱ ግብር ጋር መተባበርም እንደ ዳታንና አቤሮን፥ እንደ ቆሬን ፥ እንደ አፍኒንና ፍንሐስ፥ እንደ ናዳብና አብድዩም መሆን ነው። በዚህን ጊዜ ለቤተክርስቲያን እንደ ሙሴ እና እንደ አሮን ያለ ሰው ያስፈልጋታል። በዖዝያን ዘመን እንደ ነበሩት ያሉ ጽኑአን የሆኑ ካህናት ያስፈልጓታል። እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ያለ ሐዋርያ ጠበቃ ሆኖ ሊቆምላት ይገባል።                                            
          ለጥፋቱ ለብቻው የሚጠየቅ ክፍል የለም፥ ሁላችንም ተጠያቂዎች ነን።  ቅዱስ ዳዊት “ሁሉ ተካክሎ በአንድነት በደለ፥ አንድስ እንኳን በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም።” ብሎአልና። መዝ ፶፪፥፫። የቤተክርስቲያኒቱ ችግር የሰነበተ እንጂ አዲስ አይደለም። ያለፉትን ሃያ ዓመታት ልዩ የሚያደርገው ግን ቤተክርስቲያኒቱ ለሁለት ተከፍላ፥ የአገር ቤት ሲኖዶስ፥ የው ጭው ሲኖዶስ፥ የሀገር ቤቱ  ፓትርያርክ፥ ስደተኛው ፓትርያርክ መባሉ ነው። በዚህ ክስተት የተጎዳችው ቤተክርስቲያኒቱ ብቻ ሳትሆን ሀገሪቷም ጭምር ናት። ክስተቱንም ይዞ የመጣው የመንግሥት ለውጥ መሆኑ ሁሉም የሚያምንበት ነው። አንድ መታወቅ የሚገባው ትልቅ ጉዳይ ቢኖር፥ የዚህች ቤተክርስቲያን ጉዳይ የአርባ አምስት ሚሊዮን ምእመናን (ሕዝብ) ጉዳይ እንጂ የጥቂቶች ብቻ አለመሆኑን ነው። የአንድ ሰው ድምፅ እንኳ ሊከበር ይገባል  በሚባልበት ዓለም ተቀምጠን የዚህን ሁሉ ሕዝብ ድምፅ አልሰማም ማለት ምንም አይጠቅምም። በመሆኑም የቤተክርስትያኒቱ ልዩነት ወደ ከፋ ደረጃ ከሚያደርስ ተግባር ተቆጥበን ለዕርቅና ለሰላሙ ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል።
          እርቅን የምንፈጽመው ፥ ሰላምንም የምናመጣው ቀድሞም ለምን ተነካን? አሁንስ ለምን እንነካለን? በሚል መንፈስ ሳይሆን በዚህ ምክንያት የሚመጣ ጉዳት ካለም ስለ ቤተክርስቲያን ብለን በመታገሥ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የታረቀን ሰላም ንም የሰጠን መከራ መስቀልን ታግሦ በመስቀል ላይ በፈጸመው ቤዛነት ነውና። እኛ በበደልን እርሱ ክሶ ነውና። ሁላችንም ልንከተለው የሚገባን መንገድ ይህ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “በድላችሁ የመጣባችሁን ብትታገሡ፥ ምስጋናችሁ ምን ድን ነው? ነገር ግን መልካም እየሠራችሁ የደረሰባችሁን ግፍ ብትታገሡ ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የምታስመሰግን ይህች ናት። ለዚህ ተጠርታችኋልና፤ ክርስቶስም እኮ ፍለጋውን ትከተሉ ዘንድ ምሳሌውን ሊተውላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአል። እርሱም ኃጢአት አልሠራም፥ በአንደበቱም ሐሰት አልተገኘበትም። ሲሰድቡት አልተሳደበም ፥ መከራ ሲያጸኑበት አልተ ቀየመም፥ ነገር ግን እውነተኛ ፍርድን ለሚፈርደው አሳልፎ ሰጠ። ከኃጢአታችን ያወጣን ዘንድ በጽድቁም ያድነን ዘንድ እርሱ ስለ ኃጢአታችን በሥጋው በእንጨት ላይ ተሰቀለ። በግርፋቱም ቁስል ቁስላችሁን ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘ በዙ ነበርና፥ አሁንም ወደ ነፍሳችሁ እረኛ እና ጠባቂ ተመለሱ።” ብሎአል። ፩ኛ ጴጥ ፪፥፳-፳፭።
          ወገኖቼ፥ ይህች ቤተክርስቲያን እስከ መቼ በልዩነት ትቀጥል? ዛሬ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በማረፋቸው ምክንያት ሌላ ፓትሪያርክ ከሾምን፥ ነገ ደግሞ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ቀናቸው ደርሶ ሲያርፉ ሌላ ፓትሪያርክ ሊሾም ነው ማለት ነው። እንዲህ እያለ ሊቀጥል ነው? “ለአንድ እረኛ አንድ መንጋ ይሆናሉ፤” የሚለውን የጌታ ቃል የት እናድርሰው? ዮሐ ፲፥ ፲፮ ። ስለዚህ በሀገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ አባቶቻችን አንድ ሆናችሁ አንድ አድርጉን። የሃይማኖት ልዩነት ሳይኖራችሁ እንደ ተለያያችሁ አትቅሩ። የተወጋገዛችሁትን ውግዘት አንሡ። ውግዘቱ ለእናንተ አልተሰማችሁም ይሆናል። እኛን በተለይም በውጭው ዓለም ለምናገለግል ካህናትና ለሚገለገሉ ምእመናን ከባድ ቀንበር ሆኖብናል። ይህንን ቀንበር ስበሩልን። የልዩነቱ ምክንያት የታወቀ ስለሆነ ያለፈውን ትታችሁ የወደፊቱን አስቡ። ዓለምን ከናቁ መናኞች የሚጠበቀው ይኽ ብቻ ነው። በሀገር ቤት ያላችሁ አባቶች ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዎስ ከሃያ ዓመታት ስደት በኋላ ወደ መንበራቸው ቢመለሱ የተከፈለው ተመልሶ አንድ እንደሚሆን፥ ልዩነቱም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደ ሚፈታ ይጠፋችኋል ብዬ አላስብም። ማን ያውቃል? ዕርቅ ይውረድ ሰላሙ ይምጣ እንጂ እርሳቸውም “እኔ ሥልጣኑን አልፈልገውም፥ በእንደራሴ ይመራ፤” ሊሉ ይችላሉ።  አንድነቱ ይምጣ እንጂ መሪው መንፈስ ቅዱስ ነው። በመሆኑም እንደ ቅዱስ ጳውሎስ “እኛ እና መንፈስ ቅዱስ ይህን ወስነናል፤” እንድትሉን እስከ መጨረሻው ተስፋ እናደርጋለን። በመሆኑም አንዳችሁ ተሸነፉና አሸንፉ፥ ወይም ሁለታችሁም  ተሸነፉና አሸናፊዎች ሁኑ። ያን ጊዜ እግዚአብሔር ቅን መሪ ለቤተክ ርስቲያን ይሰጣታል። ቤተክርስቲያኒቱም የጸጥታ ወደብ ፥ የሰላም ማማ ትሆናለች። አባቶቻችንም በጥቅምትና በግንቦት ሲኖዶስ ይታይ የነበረው የእርስ በርስ ሙግት ይቀርላችኋል ። እኛም አባቶቻችን ተሰባስበው ተጨቃጨቁ ከሚለው ሰቀቀን እንድናለን። ሃይማኖት አጽንተው ሥርዓት ወስነው አስተዳደሩን አስተካክለው በፍቅር ተለያዩ ብለን በአራቱም መዓዝን እንሰ ብካለን። እናንተም በሚቀጥለው ስብሰባ እስክትገናኙ ትነፋፈቃላችሁ። እንዲህ ሲሆን በመካከላችሁ ነፋስ አይገባም። ማንም ተነሥቶ ቀን ከፈለኝ ብሎ “ጳጳሳቱ አይረቡም” አይላችሁም። ዓለም ይፈራችኋል እንጂ አትፈሩትም። “እምነ መንግሥት የዓቢ ክህነት” ትሉታላችሁ። እንደ አባቶቻችሁ አራዊቱ እንኳን ይታዘዙላችኋል። ልዑላን ትሆናላችሁ። ስለሆነም፥ ለራሳ ችሁም፥ ለቤተክርስቲያናችሁም፥ ታሪክ ሠርታችሁ እለፉ፥ እኛንም የአባቶቻችንን ገድል ለመጻፍ የበቃን እንሆን ዘንድ አድርጉን። ይህ ካልሆነ ግን አድሮብን የሚኖር መንፈስ ቅዱስ ያዝንብናል።  ኤፌ ፬፥፴።
የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን።

70 comments:

 1. Bihonln tru neber. Neger gin Abatochachin endih maseb tesanachew. Bilew bilew demo Egna kemengist enibelalen wey alun. Amlakn ke mengist gar yemiyawedadru Abatoch tefeterulin. Yemibejewun ye Dingil yilakilin.

  ReplyDelete
  Replies
  1. የቀሲስ ደጀኔ ሀሳብ በጣም የሚስማማና ተገቢም ማመልከቻ ነው። ነገር ግን ማን ነው ለማመልከቻው አዎንታዊ መልስ የሚሰጠው ነው ? የሰላሙ ቤት እንዲከፈት አርኅው ኆኃተ መኳንንት=መኳንንት በሮችን ክፈቱ ሲባል ቁልፉን የያዘው ክፍል ፈቃደኛ ሁኖ ኑ ግቡ ይላል ወይ ነው ? ሰላምን ፥ ፍቅርንና አንድነትን የሚፈልጋቸው ምን አይነት መንፈስ በውስጡ ሁኖ የሚመራው ነው ? ያም ሆነ ይህ ቀሲስ ''ዘቦ እዝን ሰሚዓ ለይስማእ'' ባለው መሠረት ጥሪያቸውን በማስተላለፍ ከአንድ ካህን የሚጠበቀውን ግዴታ ተወጥተዋል። ''ንሕነ ንነግር ወንሕነ ኢንዘብጥ=እኛ እንናገራለን እንጅ አንደባደብም'' እንዳሉት ነውና !

   Delete
  2. ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።
   ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥
   ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥
   ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤
   የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። 2ኛ ጢሞ 3፣1-5

   Delete
 2. ቃለ ህይዎት ያሰማልን አባታችን መላከ ሰላም።
  አባቶቻችን ብጹዓን ጳጳሳት፡- አንዳችሁ ተሸነፉና አሸንፉ፥ ወይም ሁለታችሁም ተሸነፉና አሸናፊዎች ሁኑ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ግሩም ብለሃል ወንድሜ አለምነው፡፡ ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ ይህ አባባል እውነት አስተውሎ ላነበበው እውን ከመንፈስ ቅዱስ የተላከ ጥሪ ነው፡፡

   Delete
  2. የሕይወትን ቃል ያሰማልን ቀሲስ ደጀኔ፡፡

   Delete
 3. nice kesis .tsegawen yabezaleh

  ReplyDelete
 4. ለመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው ቃለ ሕይወትን ያሰማልን። አምላካችን ለሁችንም መልካሙን ቅን ለቦና እነዲያድለን እንዲሁም ቤተክርስቲያንን እነደ እኛ ሐጥያት ሳይሆን ወደር በሌለው ቸርነቱ ይጠብቅልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን።

  ReplyDelete
 5. kale hiwet yasemaln, Melake Selam Amlak Ethiopian bechernetu yigobgnat.

  ReplyDelete
 6. kale hiot yasemalen kesis

  ReplyDelete
 7. Kale Hiwot Yasemalin. Amen, Yihunlin.

  ReplyDelete
 8. ቃለ ህይዎት ያሰማልን አባታችን መላከ ሰላም

  ReplyDelete
 9. Abatochachin eko wonbedewoch honewal. mi'emenanin letekula asalifew yemisetu gefiwoch nachew. Egziabher yifaredachew

  ReplyDelete
 10. ቀሲስ "መንግስታት በተለዋወጡ ቁጥር በተፅዕኖ ቀኖና ቤተክርስቲያን እየፈረሰ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው።" ያሉት ገሃድ ነው። ግን ችግራችን መንግስት ተፅእኖ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን ዋናው በፈተና ጊዜ በፅናት እሚቆም ባለመገኘቱ ነው። እስኪ የአቡነ ቴዎፍሎስን ሁናቴ እንይ- ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በሃሰተኛው የደርግ “ተሃድሶ ኮሚሽን” ተወንጅለው ለስራት ከመዳረጋቸው በፊት አንዳንድ ወዳጆቻቸው እንዲሸሹ መክረዋቸው ነበር። ቅዱስነታቸው ግን የሚደርስባቸውን ማንኛውንም መከራ ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ቆርጠው ስለነበረ ምክሩን አልተቀበሉትም፤
  እኔ አሉ ቅዱስነታቸው “ እኔ ከዚህ ደረጃ የደረስሁት ከትቢያ ተነስቼ ነው። በሰላሙ ጊዜ ስሾም ስሸለም አባ! አባታችን! እየተባልሁ ስከበር ኑሬአለሁ።ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ከንጉሰ ነገስቱ ጀምሮ ያሉ ታላላቅ ሰዎች እየታሰሩ ያለ ፍትህ እየተገደሉ ናቸው እኔም በሃገሬና በቤት ክርስቲያን ስም የሚደርስብኝን ማንኛውንም መከራ መቀበል እንጂ መሸሽ ተግባሬ አይደለም። አባቶቼ ሃዋርያትና ሰማእታት ሰለ ቀናች ሃይማኖታቸው ሲሉ በሰይፍ ተቆርጠው፤ በገመድ ታንቀውና በእሳት ተቃጥለው በሰማእትነት ተሰውተዋል፤ እኔም እንደነሱ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤት ክርስቲያን ክብር ስል እስከ ሞትም ድረስ ቢሆን መከራና ስቃይ ከመቀበል በቀር ወደ ኋላ የምልበት ምክንያት የለም።
  ቀደም ሲል በነአቡነ ጴጥሮስ ላይ የደረሰውን የሰማእትነት ሞት እኔም የነሱን ፅዋ ቆርጨ እንድቀበል እንጂ እንድሸሽ አይገፋፋኝም፤ ለእኔ ህይወት ሲባል በብዙ ድካም የተገኘውን የቤተ ክርስቲያን ክብር አላዋርድም፤ ባንገቴ ላይ ስለት (ሰይፍ) እያንዣበበ እንደሆነ ይታወቀኛል፤ ቢሆንም እዚሁ ሁኜ የሚመጣብኝን መከራ ለመቀበል ዝግጁ ስለሆንኩ በምንም ተአምር አልሸሽም” ነበር ያሉት። እንግዲህ ትልቁ ነጥብ ለተፅእኖ፤ ለፈተና እማይንበረከክ እረኛ መኖሩ ማረጋገጥ ነው። የተቀረው እዳው ገብስ ነው።
  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰላም ለሁላችሁም ይሆን። ከላይ ማንነትዎን ለመግለጽ ያልደፈሩት ወገን እኔ እንደተረዳሁት የሚሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በመሰደድ ፋንታ እንደ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ መሞት ነበረባቸው ነው ። የአባባላቸውን አንድምታ በስፋት ስንረዳው፥ እርሳቸው ቢሞቱ ኑሮ የአባ ጳውሎስ ፕትርክና ሕጋዊነቱ አጠያያቂ አይሆንም ነበር ማለታቸው ነው። ለመሆኑ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የተሰደዱት እነ አቶ መለስ በኢትዮጵያ ውስጥ ክርስቲያኖች ክርስቶስን ማምለክ አይችሉም ፤ ካመለኩ አንገታቸው በሰይፍ እየተቆረጠ ይገደሉ፥ አብያተ ክርስቲያናቱም የጣዖት ቤት ይሁኑ የሚል አዋጅ በማወጃቸው ነው መንጋውንና ቤተ ክርስቲያናቸውን ለአላውያን ነገሥታት ትተው የራሳቸውን ሕይዎት ለማዳን ከመስቀሉ የሸሹት ? የትኛው ወንጌል ላይ ነው አንድ የቤተ ክርስቲያን ኣባት የሚሥራበትን መሥሪያ ቤት ልቀቅ ሲባል አለቅም ብሎ መሞት አለበት የሚለው ? እኔ የማነበው ወንጌል ግን እንዲህ ነው የሚለው ፤<> ማቴ. 10 ፤ 23. በዚህ መሠረት ነው ቅዱስ አባታችን መንፈሳዊ ሥልጣናቸውን ሳይሆን መስሪያ ቤቱንና ምድራዊ አገራቸውን ለቀው ወደሌላይቱ ምድራዊት አገር የሸሹት። መሞት ነበረባቸው የሚለው መከራከሪያ ሐሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ መሰረት የለውም። እንዲያው ብቻ አንዳንዶቻችን በመንደርተኝነት በሺታ ስለተለከፍን 'የእኛ ' ከምንለው መንደር ካልተወለደ ለሀቅ መቆም ስለሚቸግረን የማይባለውን ለማለት እንገደዳለን እንጂ ። ይህ ደግሞ መንፈሳዊነት ሳይሆን በመንፈሳዊነት ካባ የተሸፈነ ሥጋዊ ወገንተንነት ነው። እኔ ግን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የዚች ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ ፓትርያርክ ናቸው ብየ ነው የማምነው። ምክንያቱም አዲስ አበባ ያለውን መሥሪያ ቤታቸውን እንጅ ቦታ የማይወስነውን እስከ ሕልፈተ ሥጋቸው ድረስ ያለውን ሥልጣናቸውን አይደለም አስረክበው የመጡት ። ሥልጣነ ፕትርክናን በቦታ የምንወስነው ከሆነ እኮ በውጭ የሚኖሩት ካህናት ሥልጣነ ክህነትም ሆነ የእኛ ክርስትና ኢትዮጵያ ውስጥ ቀርቶአል ማለት ነው። ሥጋዊ የሆነ ሥልጣን እንጅ በአንድ አገር ውስጥ የሚወሰነው መንፈሳዊ የሆነው ሥልጣንና እምነት አይደለም። እረ ባካችሁ ለእውነት እንቁም ! እረ ተው ከመንደርተኝነት በሺታ እንፈወስ !

   Delete
 11. ነበር ባይሰበር ሆነ እንጂ ነገሩ
  የተሾሙበት ይህ ነበር ምስጢሩ
  ቃለ ሕይወት ያሰማልን ቀስስ

  ReplyDelete
 12. አሜን ቃለ ሕይወት ያሰማልን። ለአባቶቻችንም ብርታቱን ይስጥልን።

  ReplyDelete
 13. ኣቡነ መርቆሬዎስ ከደርግ ጋር ኣብሬ ያገለገልኩት የበቅኛል። ከእንግዲህ ወድያ ሥልጣን ኣልፈልግም ብለው ኣገራቸውንና ሃላፊነታቸውን ጥለው ሸሹ። ኣሁን በግድ ሥልጣን ላይ ተቀመጡ የምትሉዋቸው ለነብሳቸው ነው ወይስ ለሥጋቸው? ሃላፊነትን የሚቀበል የሃኢማኖት ኣባት በቀውጥ ቀን ኣገሩን፤ ምዕመናኑን ፤ ሃልፊነቱን ጥሎ የሚፈረጥጥ የሃይማኖት ኣባት ሊሆን ኣይችልም። ሌላ መንግስት ሲመጣ እንደገና ጥለውን ሊሽሹ ነው? እኚሁ ኣባት የስደት ዶላር ለምደዋል። ካሁን ወድያ ከመረጡት ቦታ በፆም በዐሎት ከመኖር ሌላ የሚበጃቸው ነገር ያለ ኣይመስለኝም። ሃይማኖትና ፖለቲካ መለየት ያቃታቸው ፈሪ ኣባት ናቸውና እግዚኣብሀር ይቅር ይበላቸው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. May God forgive you for the absolute lie you are telling.

   His Holiness Abune Merkorios did not leave his position willingly or for health reason. That was a lie told by some bishops and repeated by people like yourself. Please watch recent program by ESAT.

   You also dare said that His Holiness is so used to US dollar. May God forgive you again. I am sure you never visit or saw His Holiness. If you did, you would see how humble and spiritual he is. He does not even eat three times as you and me do.

   May God reveal the truth and the light for you to tell only the truth.

   Delete
  2. Mr. Hailu, I agree with you "May God reveal the truth". As far as your statements towards Kesis Dejene stating "You also dare..." You aught not your self speak to a Kahen in this manner. You see you are accusing Kesis Dejene of not respecting Abune Merkorios, but you are not respecting Kesis Dejene in your speech towards him. If you feel Kesis is disrespectful then you should not as a Christian approach him in like manner.
   Also you say how dare you to Kesis about "lying" about a bishop, but you yourself accuse other bishops of "lying". You see this is why from the Christian point of view your arguements are weak.
   In short, let us for all intensive purposes say that there the church canon law was broken in Addis Ababa, this does not give Abune Merkorios, and the other bishops the right to create their own synod. Two wrongs will never make a right my friend. AND FINALLY WE WILL NOT FORGET THE CHURCH CANNON LAW WAS NOT BROKEN IN BITSUE ABUNE PAULOS' TIME BUT DURING TIME OF IMPRISIONMENT OF BITUSE ABUNE TEWOPHOLOS' AND ENTHRONEMENT OF BITSUE ABUNE TEKLEHAYMANOT. THATS THE BEGINNING. THINGS NEED TO GET RIGHT THERE, THE TRUTH IS THERE.

   Delete
  3. you are not understanding the reason of his exile.You are simply shouting!

   Delete
 14. Wey alemetadel yete yedersal yetebaale...enesun yategebachew memenanu new kenesu gar le hulet tekefelo beretu eyale. teketay bayenorachew yet yederesalu? egna yemenawekew abatoch fetena segetemachew wed gedam gebetew endemeseleu new. yezarewochu gin gedamachew USA hono new gera yegebachew.tegab yemayametaw yelem gena bezu yesemal.

  ReplyDelete
 15. ይህ ካልሆነ ግን አድሮብን የሚኖር መንፈስ ቅዱስ ያዝንብናል >> እግዚአብሔር ለአባቶቻችን የቀናውን መንፈስ ያድልልን "" ቃለ ሕይወትን ያሰማልን ቀሲስ

  ReplyDelete
 16. አሜን ቃለ ሕይወት ያሰማልን:: However, I doubt if the so-called church fathers can listen to your plea. The dreaded may be inevitable. It is really sad to see the EOTC being divided along such lines.

  ReplyDelete
 17. Endhi tilaleh biye altebekum neber Aba Merkoriyos endet memeles yichlalu.Esachew kengideh beqtoachewal endetekebru be tsolot tewesnew binoru new yemishalew.Betekristiyan yetmare Abat yasfelgatal

  ReplyDelete
  Replies
  1. You advocat anarchy in the church.

   The point is that lets fix the problem that created the division in our church.

   The division came about because of the illegal removal of His Holiness Abune Merkorios and assignment of "5th patriarch" against the canon law of the Church.

   Live this error uncorrected, it will serve as a precedence for any powerful to claim the position of patriarchate in the future.

   Let the 4th Patriarch return to his rightful place and peace reign in our church.

   Delete
  2. Mr. Hailu, again the "problem" is not with the enthronement of the 5th Patriarch but with the 3rd Patriarch. So to truly solve the problem that is where we have to go. When choosing a Patriarch you dont base it human calculations and will, BUT ONLY ON GOD'S WILL. And really, my friend, you seem close to Abune Merkorios, honestly, is he in the physical and mental position to lead the church of Ethiopia? If this situation was not present would he really but eligible to be Patriarch? OR IS IT JUST OUR HUMAN WILL THAT WHATS THIS? Just ask yourself, do I want God's will or my own? If we all hold on to our own wills and not yield to God then we will be punished continually until we repent. Lets just let GO! Let the HOLY SPIRIT choose for us, lets not let our PHD's and other titles whether clerigical or secular brainwash us into thinking we know better than others. The Church needs God's guidance, for this to happen we cannot have people who own want their own will to be respected, one side needs to give it up. If not God will give us up to our stubborness, and it will be hell to pay.

   Delete
  3. Yes, 'Man proposes but God disposes!'Who will come next is already decided by Him. No more conflict/worry.

   Delete
 18. egzybhere melkemun ymetea

  ReplyDelete
 19. ለመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው ቃለ ሕይወት ያሰማልን::የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን።አሜን

  ReplyDelete
 20. ለእኔ ህይወት ሲባል በብዙ ድካም የተገኘውን የቤተ ክርስቲያን ክብር አላዋርድም፤ ባንገቴ ላይ ስለት (ሰይፍ) እያንዣበበ እንደሆነ ይታወቀኛል፤ ቢሆንም እዚሁ ሁኜ የሚመጣብኝን መከራ ለመቀበል ዝግጁ ስለሆንኩ በምንም ተአምር አልሸሽም” ነበር ያሉት። እንግዲህ ትልቁ ነጥብ ለተፅእኖ፤ ለፈተና እማይንበረከክ እረኛ መኖሩ ማረጋገጥ ነው። የተቀረው እዳው ገብስ ነው።

  ReplyDelete
 21. አባታችን መልዐከ ሠላም ቀሲስ ደጀኔ ቃለ ሕይወት ያሰማልን ረጅም እድሜና ጤና ይስጥልን :: እግዚአብሔር አምላክ እንደ ኃጢአታችን ብዛት ሳይሆን እንደቸርነቱ ብሎ ለአባቶቻችን ሰላምና ፍቅር ለቤተክርስቲያን አንድነትን ይስጥልን::

  ReplyDelete
 22. በሀገር ቤት ያላችሁ አባቶች ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዎስ ከሃያ ዓመታት ስደት በኋላ ወደ መንበራቸው ቢመለሱ የተከፈለው ተመልሶ አንድ እንደሚሆን፥ ልዩነቱም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደ ሚፈታ ይጠፋችኋል ብዬ አላስብም። Very funy one...the last time I saw he was in Eriteria with ARBEGNOT fighters??

  ReplyDelete
  Replies
  1. Just to keep the records straight, Abune Merkorios has never been in Eritrea since he left Ethiopia. The bishop you saw is Abune Mekarios, not Abune Merkorios.

   Delete
  2. This is the politics of "Woyane"

   Delete
  3. Please "Woyane", Don't mess! This is religion; not your dirty game.

   Delete
  4. የዚች ቤተክርስቲያን ሰላምና አንድነት የሚመጣው በቤተክርስቲያን ውስጥ የፖለቲካ አጀንዳ ማራመድ ሲቀር ብቻ ነው:: ሁሉም የሚቀበለው አዲስ ፓትርያርክ መምረጥ ቢቻል ጥሩ ነበር:: ዋነኛ የቤተክርስቲያን በሽታዎች የቀደሙት ሁለቱ ፓትርያርኮች ናቸው:: አባ መርቆርዮስን መመለስ ሌላውን ችግር መፍጠር ነው:: ለነገሩ ሊሆንም ስለማይችል ጎንደሮች ተስፋ ብትቆርጡ ይሻላል:: እዚያው በስደተኛነታቸው ሰላም ሆነው እኛን ግን ሰላም ነሰተው ይቀመጡ::

   Delete
 23. "በሀገር ቤት ያላችሁ አባቶች ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዎስ ከሃያ ዓመታት ስደት በኋላ ወደ መንበራቸው ቢመለሱ የተከፈለው ተመልሶ አንድ እንደሚሆን፥ ልዩነቱም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደ ሚፈታ ይጠፋችኋል ብዬ አላስብም።" ቀሲስ ደጀኔ የእርስዎም አስተያየት እኚህ ሰው ወደ ስልጣን ይመለሱ የሚል ነው? ታዲያ ማነው ቤተክርስቲያንን ከግለሰብ የሚያስቀድም? ይህ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አጀንዳ መሆኑን ለይተው ያወቁት አልመሰለኝም:: እርስዎ በወንጌሉ ላይ ቢያተኩሩ መልካም ነው::

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ato Sim Aytere,

   This is the most important issue of our church. It is not an agenda of any opposition group. We are talking about our church. Our church was divided because of the illegal removal of the 4th Patriarch against the age old canon law of our church. We are discussing to once again unite our church. And the way to do that is to Right the Wrong by returning His Holiness Abune Merkorios to his rightful place in Ethiopia. This is not politics, this is a matter of our faith.

   Delete
 24. yabune pawlosem gedam america neberech.hulun neger ketekawami agenda gar magenagnet denkurena new.degmos tekawamiwoch lehager yemitekem agenda yelachewem belo yewesene manew?yehager betwan betekrestiyan yemimerat weyane endehone eko enawkalen.melektun bepoletica menetser sayhon behaymanot menetser aytehew kehone egzeaheberem ewnetegnochu kerestiyanochim yemikebelut new.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተቃዋሚ መሆን አይጠቅምም የሚል የለም:: ለምን ቤተክርስቲያን ውስጥ ይመሽጋል? ነው ጥያቄው:: ስደተኛ 'ሲኖዶስ' ውስጥ መሽጎ አሁን ደግሞ ይመለሱ በሚል ሰበብ አዲስ አበባ ባለው ሲኖዶስ በሰፊው ለመንቀሳቀስ አስቦ ነው:: ይህ ደግሞ ቤተክርስቲያንን የጦርነት መድረክ ማድረግ ነው:: ወያኔ ይሻለናል ለማለት ሳይሆን አሁን ያለው ብጥብጥ ይበቃናል ለማለት ነው:: ተቃዋሚዎች እባካችሁ ከቤተክርስቲያን ጥገኝነት ውጡ:: ህዝቡን ለማገኘት ሌላ መድረክ እንደሌላችሁ እናውቃለን:: ግን ለእዚአብሄር ብላችሁ አድርጉት:: እግዚአብሔርን በነጻነት እናምልክበት:: የእኛ አላማ መሆን ያለበት አዲስ አበባ ካለው ሲኖዶስ ወያኔን ማስወጣት እንጀ ተቃዋሚን ማስጠጋት አይደለም::

   Delete
 25. ቃለ ህይዎት ያሰማልን አባታችን።

  ReplyDelete
 26. G/Silassie: By theway leaving when somebad thing happened on the church was Egypitians Fathers practice not Ethiopians but it happened by Abune Merkorios, I feel still so sad because we had been begging so long to get our own Patriarch and we succeded on that but now it looks like we like to have someone from Egypt or "U.S.A". So I did not blame The Ethiopian Holy synod members when they said Abune Merkorios can not get back to that position, however if this is the only way to get back our Church unity, I will say yes only for our unity purpose not for AbunebMerkorios Confort. Anyway Kesis Dejenen Kalehiwot Yasemalin.

  ReplyDelete
 27. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ቀሲስ! ለአገልግሎት ረጅም ዕድሜ ያድልልን!! ሁሉንም በሚገባ በሚያንጸው በእግዚአብሔር ቃል ብቻ ተንተርሰው አስቀምጠውታል። ከዚህ የቀረው እንግዲህ ዓይን ያለው ያስተውል ጆሮ ያለው ይስማ የሚል ብቻ ነው። የሚያስተውልና የሚሰማ ከጠፋ እርስዎ አሳምረው እንደጠቀሱት ያልሰማ ለራሱ ይብሰበታል እንጂ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይራራልና የርሱን ቸርነት ብዙም ሳይቆይ እንጠባበቃለን። እግዚአብሔር በጸጋ ላይ ጸጋ ያብዛልዎት!!!

  ReplyDelete
 28. It is the right comment .Fathers of addis they never look far.they are corrapted and never have care about orthodx people.

  Alem

  ReplyDelete
  Replies
  1. "Thy shall not judge, for with the same measure you shall be judged." You accuse of the fathers corruption, but your statement is corrupt as well with judgements and accussations which is against what our Lord taught us. If we are people of peace, then our statements will be peaceful

   Delete
 29. ዓለም ይፈራችኋል እንጂ አትፈሩትም። “እምነ መንግሥት የዓቢ ክህነት” ትሉታላችሁ።

  ReplyDelete
 30. mengedachiu ke mengede hasbchhu ke hasabe ye teleye new ylal ye EGZABHER kal esu be meknyat wede sidet yametachew, be wich hager yale Ethiopian hezb or memenan le wengel agelglot sile azgageln new. yesewn
  sira bicha sayhon ye EGZIABHERNIM sira mermru

  ReplyDelete
 31. Kale-hiwot yasemalin !!

  ReplyDelete
 32. Sint ayinet sew all???Keabune PAWLOS yebelete kadire poletikegna neber ende?lemin ayinachin yayewen lemeshefen enmokralen?sint deha yenebite teremamidew SHRATEN yewalu yemejemriyaw modern menkuse.Abune MERKORIWOS yegid tegefitew kemnberachew siwerdu tadiya gedam weyim washa teshkimew meseded neberbachew?mesewat lemhonim Eko yemisewh menor alebet.yihe kalenga, sew kalenga zer yelem yemilut beye-timihiritbetu,beye-mesriyabetu yeselechen gotenginet ezihim megelamet jemere?Lehulum Egziabher yiridan! KESIS QALEHIYIWOTEN YASEMALEN.

  ReplyDelete
 33. አባቶቻችን ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፡- አንዳችሁ ተሸነፉና አሸንፉ፥ ወይም ሁለታችሁም ተሸነፉና አሸናፊዎች ሁኑ።

  ReplyDelete
 34. Thank you very much Kesis for your golden ideas, suggestion and advise. This is the right and excellent stand I am waiting for long time from all EOTC preachers. I wish the other preachers of the EOTC would tell us their firm stand at this critical and historical time of our church.

  ReplyDelete
 35. አባታችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
  አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ የአባቶቻችንን ልብ አለዝቦ
  ልዩነታቸውን አስዎግዶ በአንድነት በፍቅር ለተዋህዶ
  ቤተ ክርስቲያናችን ለተዋህዶ ሃይማኖታችን የሚቆሙ
  ያድርግልን።

  የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት አይለየን።
  አሜን።

  ReplyDelete
 36. አበው ተመከሩ፦
  በተቻለ መጠን ከሁሉ በፊት ለሰላም ፍጠኑ የሰላምን ሸማ ተጎናጸፉ የጸብን ግድግዳ ሌላ ማንም መጥቶ ሊያፈርስ አይችልም እናንተው ናችሁ የሁሉም ነገር ጊዜው አሁን ነው ይህን ወቅት በማስተዋል እና በትዕግስት ካለፋችሁ ለትውልድ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ታስተላልፋላችሁ በተቃራኒው ደግሞ የሚሆነውን ልባችሁ ያውቀዋል ትውልድ እና ታሪክ ኅሊናችሁም ሁሌ እስታልፉ ደረስ እየወቀሳችሁ ለዘለዓለም ይኖራልይህ ከመሆኑ በፊት አባቶቻችን ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፡- አንዳችሁ ተሸነፉና አሸንፉ፥ ወይም ሁለታችሁም ተሸነፉና አሸናፊዎች ሁኑ። ከመንፈስ ልጀችሁ ቀሲስ ነኝ

  ReplyDelete
 37. ቀሲስ በእግዚአብሔር ቃል የተመላ ምክር አስተላልፈዋል። እንዲህ ነው ከእውነት ጎን መገኘት ምስክርነት በሚያስፈልግበት ጊዜ! ጸጋውን ያብዛልዎት! "ቀን ከፈለኝ ብሎ" ያሉት ቀን ሰጠኝ ብሎ ተብሎ ቢስተካከል ጥሩ ሳይሆን አይቀርም የሚል አስተያየት አለኝ። ምክንያቱም "ከፈለኝ" የሚለው ሥራ ሠርቶ ዋጋው ሳይከፈለው ተበድሎ የቆየ ሰው የነበረና አሁን ጊዜው ሲደርስ ክፍያውን ያገኘ ያስመስለዋል። የርስዎ ሀሳብ ይህ አይመስለኝም። "ቀን የሰጠው" ግን ይህ ነው የሚባል ምክንያት ሳይኖር አጋጣሚ ሁኔታዎችን ያመቻቸለት ማለት ስለሚሆን የበለጠ ሀሳብዎን የሚገልጸው ይመስላል - "ማንም ተነሥቶ ቀን ሰጠኝ ብሎ 'ጳጳሳቱ አይረቡም' አይላችሁም"። ዕድሜዎን ያርዝምልን!

  ReplyDelete
 38. አለማወቃችሁን እግዚአብሄር ይቅር ይበላችሁ፡ የቤተክርስትያን ጉዳይ እኮ የጽድቅ እና የኩነኔ ጉዳይ ነዉ፡ ስለዚህ ሁሉም ክርስትያን በ ከፋፋዮች እና በዘረኞች ሳይደናገር የቤተክርስትያንን አንድነት መጠበቅ ይገባል። ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪወስ በሚያሳዝን ሁኔታ በመንግስት ጣልቃ ገብነት እንደተሰደዱ ለማንም ግልጽ ነዉ፡እኒህ አባት እኮ 21 አመት ሙሉ በጸሎት እና በዝምታ የአለምን ነገር በመተዉ ለእግዚአብሄር ሁሉን ሰጥተዉ በእግዚአብሄር ፈቃድ የሚኖሩ ናቸዉ፡የተሰደዱትም ለእዉነት እና ለጽድቅ ሲሉ ነዉ፡ ፓትርያሪክ በህይወት እያለ ሌላ እንዳይሾም ፍትሀሃ ነገስቱ ይደነግጋል፡ አሁንም ቢሆን ያለፈዉን ስእተት አርመን እና የተጣሰዉን ቀኖና አስተካክለን የመጭዉን የቤተክርስትያን ሁኔታ ለጳጳሳቱ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የእምነቱ ተከታይ ስለሀይማኖቱ ሊነሳ ይገባዋል።አንዳንድ አላዋቂወች የቤተክርስትያን ጉዳይ የነብስ ጉዳይ እንደሆነ ባለማወቅ ወደ ፓለቲካ እና ወደብሄር ሊያጠጋጉት ይሞክራሉ፡

  ReplyDelete
 39. አንዳችሁ ተሸነፉና አሸንፉ፥ ወይም ሁለታችሁም ተሸነፉና አሸናፊዎች ሁኑ።

  ReplyDelete
 40. ከልጅነት እስከ እውቀት የሰበኩን አባቶች በተግባርም ሊያሳዩን ቀን መጣላቸው!

  ReplyDelete
 41. ቀሲስ ክህነትህን አከብራለሁኝ ነገር ግን የግል ጥቅማቹ በልጦባቹ በየውጭ ሀገራቹ ተቀምጣቹ ይችን በቀደሙ አባቶቻችን ፆም እና ፀሎት እንዲሁም በደማቸውን ያቆያትን ሃይማኖት እናንተ እጅ ላይ ወድቃለች፡፡ እንዴት እድርጋቹ ለትውልት እደምታስተላልፉት ግን ጌታዬ ስላሴ ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡ ቅድስት ድንግል አገራችንን ሃይማኖታቸንን ትጠብቅልን፡፡

  ReplyDelete
 42. What Do you think about the decition of destroying EOTC by alleged mad Government today (08/05/05). The pops are not real pops!

  ReplyDelete
 43. አባታችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
  አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ የአባቶቻችንን ልብ አለዝቦ
  ልዩነታቸውን አስዎግዶ በአንድነት በፍቅር ለተዋህዶ
  ቤተ ክርስቲያናችን ለተዋህዶ ሃይማኖታችን የሚቆሙ
  ያድርግልን።

  የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት አይለየን።
  አሜን።

  ReplyDelete
 44. i am just tired of the word "ABATOCH" who is abat?

  ReplyDelete
 45. አባታችን በቅድሜ ቃለ ሔወት ያሰማልን : እንግዲህ በያላችሁበት ሁናችሁ ቄሶች አባቶቾ ዴያቆናት ወንድሞች: እንዲሁም የበተክርስቴያን ልጆቾ ሰባኬያንና ዘማሪያን በሙሉ :በመሰባሰብ ለምእመኑ በያለንበት ቁመን ታሪክ ለዋጭ አምላክን እንድለምን የናንተ እርዳታ ከመቸውም በላቀ የሜያስፈልገን ይመስለኛል።በእድሜየ በተክርስቴያንና ምእመን አንገታቸውን የደፎበት ወርህ ካለ ይኸው ወርህ ጥር ነው። የአባቶች ነገርማ !!!

  ReplyDelete
 46. አለማወቃችሁን እግዚአብሄር ይቅር ይበላችሁ፡ የቤተክርስትያን ጉዳይ እኮ የጽድቅ እና የኩነኔ ጉዳይ ነዉ፡ ስለዚህ ሁሉም ክርስትያን በ ከፋፋዮች እና በዘረኞች ሳይደናገር [በመጀምሪያ ከላይ ኮመንት የሰጠሽው ሂሩት ከሁሉ በፊት ከአምስቱ የስን ምግባር ስርአት አንዱ አንጋገር ብሞሆኑ ታረሚ። ጌታ አሮንና ማርያምን የተቆጣው ካህኑን ሙሴን ሲያሙ ስለነበረ ነው።]የቤተክርስትያንን አንድነት መጠበቅ ይገባል። ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪወስ በሚያሳዝን ሁኔታ በመንግስት ጣልቃ ገብነት እንደተሰደዱ ለማንም ግልጽ ነዉ፡እኒህ አባት እኮ 21 አመት ሙሉ በጸሎት እና በዝምታ የአለምን ነገር በመተዉ ለእግዚአብሄር ሁሉን ሰጥተዉ በእግዚአብሄር ፈቃድ የሚኖሩ ናቸዉ፡የተሰደዱትም ለእዉነት እና ለጽድቅ ሲሉ ነዉ፡ ፓትርያሪክ በህይወት እያለ ሌላ እንዳይሾም ፍትሀሃ ነገስቱ ይደነግጋል፡ አሁንም ቢሆን ያለፈዉን ስእተት አርመን እና የተጣሰዉን ቀኖና አስተካክለን የመጭዉን የቤተክርስትያን ሁኔታ ለጳጳሳቱ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የእምነቱ ተከታይ ስለሀይማኖቱ ሊነሳ ይገባዋል።አንዳንድ አላዋቂወች የቤተክርስትያን ጉዳይ የነብስ ጉዳይ እንደሆነ ባለማወቅ ወደ ፓለቲካ እና ወደብሄር ሊያጠጋጉት ይሞክራሉ፡፡
  ብቻ አምላክ ልቤቱ ያስባልና እርሱ ሰላሙንና አስተዋይ አባት ይስጠን አሜን!!!

  ReplyDelete
 47. አለማወቃችሁን በትለይ ከላይ ኮሜንት የሰጠሽው ሂሩት እግዚአብሄር ይቅር ይበላችሁ፡ የቤተክርስትያን ጉዳይ እኮ የጽድቅ እና የኩነኔ ጉዳይ ነዉ፡ ስለዚህ ሁሉም ክርስትያን በ ከፋፋዮች እና በዘረኞች ሳይደናገር የቤተክርስትያንን አንድነት መጠበቅ ይገባል። ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪወስ በሚያሳዝን ሁኔታ በመንግስት ጣልቃ ገብነት እንደተሰደዱ ለማንም ግልጽ ነዉ፡እኒህ አባት እኮ 21 አመት ሙሉ በጸሎት እና በዝምታ የአለምን ነገር በመተዉ ለእግዚአብሄር ሁሉን ሰጥተዉ በእግዚአብሄር ፈቃድ የሚኖሩ ናቸዉ፡የተሰደዱትም ለእዉነት እና ለጽድቅ ሲሉ ነዉ፡ ፓትርያሪክ በህይወት እያለ ሌላ እንዳይሾም ፍትሀሃ ነገስቱ ይደነግጋል፡ አሁንም ቢሆን ያለፈዉን ስእተት አርመን እና የተጣሰዉን ቀኖና አስተካክለን የመጭዉን የቤተክርስትያን ሁኔታ ለጳጳሳቱ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የእምነቱ ተከታይ ስለሀይማኖቱ ሊነሳ ይገባዋል።አንዳንድ አላዋቂወች የቤተክርስትያን ጉዳይ የነብስ ጉዳይ እንደሆነ ባለማወቅ ወደ ፓለቲካ እና ወደብሄር ሊያጠጋጉት ይሞክራሉ፡

  ReplyDelete
 48. ቅዱሳን አባቶቻችን በቤተክረስቲያናችን ላይ ችግር ፈተና ሲገጥማቸው የተቀመጡት በአገራቸው ገዳም ውስጥ በፆም በፀሎት ነው፡፡ የግብፁ አቡነ ሸኖዳም በገጠማቸው ፈተና በአገራቸው ገዳም ነው የተቀመጡት በጥሞና እና በፆም በፀሎት ነው ያሳለፉት፡፡ቅድስት ድንግል ማርያም አገራችንን እና ሃይማኖታችንን ትጠብቅልን፡፡

  ReplyDelete