Thursday, July 26, 2012

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስና ትምህርታቸው፤ ክፍል አንድ


ጳጉሜን ፩ ቀን ፲፱፻፹፪  ዓም የወጣው ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ መልኩም ሆነ ዜናው ከወትሮው ለየት ያለ ነው። መልኩ የወየበ ደም ይመስላል።አትኩረው ሲያዩት ከበሰለ ወይን ወይም ከገረጣ ሐምራዊ ቀለም ጋር አንድ ነው። መልሶ መላልሶ ላስተዋለው በሦስቱም መልክ ሆነ በአንደኛው የጌታን ክቡር ደም ያስታውሳል።በቀራንዮ የፈሰሰውን የክርስቶስን ደም በኅሊና እየሳለ የመሥዋዕትነትን ቅዱስነት፣ በለሆሳስ የሚያስተላልፍ ድምፅ ከወረቀቱ ግዘፍ ነስቶ ይሠርፃል። ከዚሁ ገጽ በቀኝ ዓምድ በኲል «ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ዐረፉ፤» የሚል ዜና በጥቁር ቀለም ሰፍሯል። መስቀሉን በቀኝ እጅ የጨበጠው ምስላቸው ምዕመናንን ይሰናበታል። 

          ዳሩ ግን ሊቀ ጳጳስ ጎርጎርዮስ ዛሬም ሕያው ናቸው።በሰዎች ልቡና፥ በገዳማት አጸድ፥ በአድባራት ዓውደ ምሕረት፥ በቅኔ ማኅሌት፥ በቅድስቱ ዙሪያና በሕገ ታቦታቱ ማረፊያ መንበር ጭምር ሐዋርያዊ ድምፃቸው ያስተጋባል። «ልጆቼ ዓላማዬን ተከተሉ፤» የሚለው አባታዊ ምክራቸው በወጣቱ ልብ በየሰንበት ት/ቤቱ፥በካህናቱና በጳጳሳቱም ዘንድ ይንቦገቦጋል።«እኛ የመነኮስነው ለፍትፍት አይደለም፥የመስቀሉ ፍቅር ይግባችሁ፤»እያሉ ከጭንጫ ላይ ሳይሆን ከጥቂት የለሰለሰ ማሳ ላይ የዘሩት ፍሬ በብዙ መነኰሳት የደም ስር ውስጥ ዛሬም ይዘዋወራል።ለእርሳቸው የነበራቸው፥ ያላቸውና ወደፊትም የሚኖራቸው ጽኑ ፍቅር፥ በቃለ እግዚአብሔር የተፈተለና የተቋጨ ነው።በመሆኑም ቢረሱት የማይረሳ፥ እፍ ቢሉትም የማይጠፋ የማለዳ ጎሕ ነው።
          ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የተገኙት በስእለት ነው።ወላጅ እናታቸው እማሆይ አሰለፈች ካሣ፥ለደሴ መድኃኔዓለም ብፅዓት ሲገቡ «የተባረከ ልጅ ከሰጠኸኝ ላንተው ቀዳሽ አደርገዋለሁ፤»ይላሉ።ለዚህም ምክንያት የሆናቸው ወንድ ልጅ አላድግ ብሏቸው ስለነበረ ነው።ከአቶ ገበየሁ ካሣዬና ከእማሆይ አሰለፈች በ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. የተወለዱት አባ ጎርጎርዮስ ወደ ተቀደሰው የእግዚአብሔር ጎዳና ያመሩት ገና በሕፃንነታቸው ነበር።ገና በአንድ ዓመት ጨቅላ ዕድሜያቸው የእንጨት መስቀል ሠርተው ለማሳለም ይሞክሩ እንደነበር ወላጅ ዘመዶቻቸው ይናገራሉ። መምህራቸው አለቃ ድንቁ በዚያ ሲያልፉ የያኔው ሕፃን የድጓውን ቅጠል እየገለጠ ሲያይ ተመልክተው «የዚህን ልጅ መዳረሻ ዕድሜ ሰጥቶኝ ባሳየኝ፤» እያሉ በመገረም ይናገሩ እንደነበር ዘመዶቻቸው በመሪር ትዝታ ያስታውሳሉ።
በሕፃን ልባቸው የመስቀሉ ፍቅር የተለኮሰባቸው አባ ጎርጎርዮስ የሀገራችንን መንፈሳዊ ዕውቀት በስፋትና በጥልቀት ገብይተዋል።ዝናቸው ከታወቀ የተለያዩ የኢትዮጵያ ገዳማት፥በብቃታቸው ከተመሰከረላቸው ሊቃውንት ዘንድ፦ ዜማ፥ቅኔ ትርጓሜ መጻሕፍት፥ባሕረ ሃሣብ፥ አጠናቀው ተምረዋል።ምሥጢር አደላድለውም ተመርቀዋል።ዘመናዊውንም ትምህርት በየደረጃው ቀስመዋል።በኋላም ወደ ግሪክ ሀገር በመጓዝ ከአቴና ዩኒቨርስቲ በነገረ መለኮት በማስትሬት ድግሪ ተመርቀዋል። ፈረንሳይኛና አረብኛ ቋንቋም አጥንተዋል፥ ግሪክኛና  እንግሊዘኛውንም የተማሩት የተማሩበት ስለሆነ ያውቁታል።
አባ ጎርጎርዮስን ልዩ በሆነና ፍቅርን በተመላ መንፈሳዊ ስሜት እንዲታሰቡ የሚያደርጋቸው አያሌ ቁምነገሮች አሉ። ዋና ዋናዎቹም ፍጹም የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎታቸው፥ ለሃይማኖታቸውም ሆነ ለሀገራቸው ቀናዒ መሆናቸው፥ እንከን የሌለው ኦርቶዶክሳዊ ትምህርታቸው፥ የምርምር ችሎታቸው፥ የሥነ ጸሑፍና የማስተማር ስጦታቸው ናቸው።
አገልግሎታቸው ሰፊና መሠረት ያለው ነው።ሦስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ በነበሩት በባሕታዊው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት አንብሮተ ዕድ ጳጳስ ሆነው ከተሾሙበት ከ፲፱፻፸፩ ዓ.ም. ጀምሮ ሕይወታቸው በመኪና አደጋ እስከ አለፈበት ሐምሌ ፳፪ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. ድረስ እጅግ ድንቅ ድንቅ የሆኑ በርካታ ሥራዎችን አከናውነዋል።ተዘግቶ የነበረውን የዝዋይን የካህናት ማሰልጠኛ እንደገና በመክፈት፥በገዳም ሥርዓት እንዲተዳደርም በማስወሰን አያሌ ካህናትን ከሦስት ክፍላተ ሀገር (ከሸዋ ከሀረርጌና ከአርሲ) በማስመጣት አሰልጥነዋል። በመቶ የሚቆጠሩ የአካባቢውን እና ከሌሎችም አካባቢ የመጡ ሕፃናትን በገዳሙ በማሳደግ መንፈሳዊውንም ሆነ ዘመናዊውን ትምህርት እንዲማሩ አድርገዋል።የቅዱስ ገብርኤልን ቤተክርስቲያን ያነጹት እርሳቸው ናቸው።የተለያዩ የልማት አውታሮችን በመዘርጋትም በረሀውን ገነት አድርገውታል።በመሆኑም መሬታዊ አካላቸው ራሳቸው ባሳነጹት በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ከመንበሩ ስር ማረፉ ያለ ምክንያት አይደለም።
ትምህርታቸው ልቡናን ሰብሮ የሚገባ፥በምሳሌዎች ፈክቶ ሕሊናን የሚመስጥና ጥልቀት ያለው ነበር።ኮለል እንዳለ የምንጭ ውኃ ቢጐነጩት የማይሰለች፥ መንፈሳዊ ፍቅርንና የጥበብን ፋና ከልብ ውስጥ የሚጭር ነበር።ከእርሳቸው የዕውቀት ማዕድ የተሳተፉ አንድ መንፈሳዊ አባት «ትምህርታቸው እንደ ዓባይ የሚቀዳ ነበር፤» በማለት ያስታውሳሉ።«ትምህርታቸው ከተዋሕዶ እምነት አማናዊ ጥልቅ ፍቅር የሚመነጭ ፍቱንና የነጠረ ቃለ እግዚአብሔር ነው፤» ይላሉ።
የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ጠባያቸውና አስተሳሰባቸው ለየት ያለ እንደነበረ በቅርብ የሚያውቋቸው ሁሉ በአድናቆት ይመሰክራሉ።ስለርሳቸው ባነሱ ቁጥር ዕንባ የሚተናነቃቸው አንድ አባት ሲናገሩ «እርሳቸው ሀገራቸውንና ሕዝባቸውን የሚወዱ፥ በኢትዮጵያዊነት የሚያምኑ፥ እናት ለልጅዋ እንደምታስብ ለሀገራቸውም ለቤተክርስቲያናቸውም የሚያስቡ፥ ሥጋዊ ጥቅም የማያታልላቸው፥ ዘረኝነት የማይደልላቸው፥ በሃይማኖታቸውም ሆነ በሀገራቸው ጉዳይ አድርባይነት የሌለባ ቸው፥ ፍርሃት የሌላቸው፥ እውነትን ብቻ የሚናገሩ ናቸው። ዕለቱን ይሞታሉ እንጂ አድርባይነትን አያውቁም፤» ይላሉ። እኚሁ አባት ስለ አባ ጎርጎርዮስ ፍጹም መንፈሳዊነት ሲናገሩ፦ «በብሕትሁና ዘመናቸው በደብረ ሊባኖስ የሰገዱበት የእጃቸው ፈለግ ሞፈር የሄደበት የበሬ ጫንቃ ይመስላል።» በማለት በተመስጦ ያስታውሳሉ።
ለወጣቶች የተለየ ፍቅርና ክብካቤ ያደርጉ እንደነበር፥ ከፍተኛ በሆነ አባታዊ አቀራረባቸው ቤተሰብ እንደሚያስረሱና ወጣቶችን «እናንተ የቤተክርስቲያን የስስት (የፍቅር) ልጆች ናችሁ፥ የሰንበት ተማሪዎች የቤተክርስቲያን ችግኞች ናችሁ።» በማለት ወጣቱን ተስፋ በተላበሰ ሃይማኖታዊ ፍቅር ይኰተኩቱ ነበር። በአንድ ወቅት የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ እርሳቸው ዘንድ በነበርኩበት ጊዜ (በ፲፱፻፸፭ ዓ.ም.) «የኔ ልጅ፥ የእኔ ዓላማ የመንግሥት ደሞዝ እየበሉ በመላው ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉ ካህንን መፍጠር ነው፤» ብለውኝ ነበር። እንደተናገሩትም ከተለያየ አካባቢ የመጡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን (ዲያቆናትን እና የሰንበት ተማሪዎችን) ክረምት ክረምት ማሰልጥ ጀመሩ። ከዓመት ዓመትም ቊጥራቸው እየጨመረ መጣ። ይህ ጅምር መቼም መች እንደማይቆም በማወቃቸውም፥ ከመሞታቸው ሦስት ቀን አስቀድሞ (ሐምሌ ፲፱ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም.) «እኔ የለኰስኲት እሳት ከእንግዲህ አይጠፋም፤» ብለዋል። እውነትም በእያንዳንዳችን ውስጥ የለኰሱት ይህ የሃይማኖት እሳት በምንም መንገድ የሚጠፋ አይደለም። በመሆኑም ማኅበረ ቅዱሳንን በሃሣብ ጸንሰው፥ በትምህርት ወልደው፥ በመንፈስ ቅዱስ እሳትነት ለኲሰው ለዚህ ያበቁት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ናቸው።
በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተምረው፦ ዲያቆናት፥ ቀሳውስት፥ መነኰሳት የሆኑ አያሌ ናቸው። በቊጥር የተወሰኑ ጳጳሳትም አሉ። ይህም የሚያሳየው ታላቁ የወንጌል ገበሬ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ዘርተው ያበቀሉ፥ ማብቀልም ብቻ ሳይሆን ሠላሳ ስድሣ መቶ ያፈሩ፥ተክለውም ያጸደቁ መሆናቸው በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነው።
በቅርብ የሚያውቋቸው መነኮሳት፥ ወጣቶችና የሥጋ ዘመዶቻቸው ጭምር በአጽንዖት ደጋግመው የሚያነሡት አንድ ዓቢይ ጉዳይ አለ።ይኸውም በወገን፥ በወንዝ ልጅ፥ በሥጋ ዘመድ አለማመናቸውን ነው፡ በአንድ ወቅት የሥጋ ወንድማቸው ዝዋይ ድረስ መጥቶ «በሀገረ ስብከትዎ የደብር እልቅና ይስጡኝ፤» ቢላቸው፥ ከሌሎቹ ለይተው ለእርሱ ሹመት ሊሰጡት እንደማይችሉ በመነኰሳቱ ፊት ነግረው አሰናብተውታል። ከዚህም የተነሣ የሥጋ ዘመዶቻቸው «የእርሳቸው ዘመድ ከመሆን ባእድ መሆን ይመረጣል፤» ይላሉ። እኛም እንደምናውቀው በዝዋይ ገዳም የሌለ የለም። ትምህርት ፈልጐ በዓላማ ይምጣ እንጂ በራቸው ለሁሉም ክፍት ነው። አባ ጎርጎርዮስ የሃይማኖትና የታሪክ ተመራማሪ ነበሩ። በሕይወት ዘመናቸው ስምንት መጻሕፍት አዘጋጅተዋል። እነርሱም፦ ፩፦ መሠረተ እምነት፤ ፪፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ፤ ፫፦ የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ፤ ፬፦ ትምህርተ ሃይማኖት (ዶግማ) ፭፦ ኦርቶዶክሳዊ የስብከት ዘዴ፤ ፮፦ ቤተክርስቲያንህን ዕወቅ፤ ፯፦ ሥርዓተ ኖሎት ፰፦ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ናቸው።
መጻሕፍቶቻቸው፦ በምርምር ላይ የተመረኮዙ፥ ጥልቅ ምሥጢር ያካተቱ፥ በውብ ቃላትና እጥር ምጥን ባለ አገላለጽ የተከሸኑ ናቸው። በተለይም የቤተክርስቲያናችንን ታሪክ በስፋት የሚያወሳው መጽሐፍ ጠቃሚነቱ እጅግ የጎላ ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ በሕገ ልቡናና በሕገ ኦሪት ዘመን፥ በኋላም የክርስትናን እምነት ከተቀበለችበት ከ፴፬ ዓ.ም. አንሥቶ እስከዛሬ የተጓዘችባቸውን ወጣ ገብ የታሪክ ሂደቶች ወለል አድርጐ ይገልጻል። መጽሐፉ የቤተክርስቲያናችንን መሠረተ እምነት፥ የታቦትን፣ የሥዕልንና የመስቀልኝ ክብር፥የአማላጅነትን ምሥጢር፥የቤተክርስቲያንን ትውፊትና ሥሪት ግልጽ በሆነ ባልተድበሰበሰ ኹኔታ አብራርቶ ያስረዳል።ኢኩሜኒዝም ወይም ዓለም አቀፍ የክርስቲያኖችን ንቅናቄ ምንነት በውል ይተነትናል፥ይልቁንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ድርሻና ተሳትፎ በግልጽ ያቀርባል። ይህ መጽሐፍ በ፩፻፺፫ ገጾች ብቻ ታሪክን ከምሥጢራት፥ መሠረተ እምነትን ከትውፊት ጨምቆና አስውቦ የሚያቀርብ ስለሆነ፥ የደራሲውን ችሎታ፥ጥልቅ አስተሳሰብና በሳል አመለካከት ይመሰክራል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ከሚለው ለአብነት ስንጠቅስ፦«አፍሪካ የጨለማ ክፍለ ዓለም ተብላ ትጠራ እንጂ ብዙ ታሪካውያን ሰዎች ተፈጥረውባታል።ብዙ የሃይማኖት ሰዎችም ነበሩባት።ነገር ግን ከጊዜ ብዛት፥ ከተተኪም መጥፋት የተነሣ ታሪኳ ሰርዶ እየለበሰ ሄደ።ሕዝቧም በልዩ ልዩ ቅኝ ገዢዎች ባህልና ሃይማኖት ስለተዋጠ ራስን የማወቅ ችግር ገጠመው። ያን ጊዜ የበግ ቆዳ ለብሶ ወደ አፍሪካ የገባው ተኲላ የብዙ አፍሪካውያንን ደም እየመጠጠ እስከ አሁን አለ።»የሚል እናገኛለን።ኢትዮጵያን አስመልክተው ደግሞ፦«ኢትዮጵያ ነፃነቷንና አንድነትዋን አክብራ አስከብራ የቆየችው፥ ለውጭ ወራሪም አልመች ያለችው በሃይማኖቷና በታሪኳ እየተከላከለች ነው።» ብለዋል። ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ከዚህ ዓለም በመኪና አደጋ በሞት የተለዩት በ፶ ዓመታቸው ነው። ከዚህ በመቀጠል በመጻሕፍቶቻቸው ላይ ያስቀመጡትን ትምህተታቸውን በተከታታይ እናቀርባለን።
                             ፩፦ መሠረተ እምነት (ዶግማ)
                         ( ምሥጢረ ሥላሴ)

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የምታምነውና የምታስተምረው እምነት በቅዱሳት መጻሕፍት በብሉይና በሐዲስ ኪዳን ከዚህም ጋር ከቅዱሳን ሐዋርያት ጀምሮ በአፍም በመጣፍም በቤተክርስቲያን ሊቃውንት በተሰጠ ትምህርት እና ትውፊት ላይ የተመሠረተ ነው። ይኸውም ቅዱስ ቄሮሎስ፦ «ሃይማኖት ርትዕት እንተ ሐዋርያትትውፊት፤» እንዳለው ነው። እነዚህንም የእምነታችንን  መሠረቶች እንደሚከተለው እንገልጻቸዋለን።

ሀ፦ በቅዱሳት መጻሕፍት፦ «ስማዕ እሥራኤል አሐዱ ውእቱ አምላክከ፤እሥራኤል ሆይ ስማ፥አምላክህ እግዚአብሔር አንድ ነው፤» ዘዳ ፮፥፬። እንደተባለ በአንድ አምላክ ማመንን ታስተምራለች።ስለዚህ ቤተክርስቲያናችን «Monotheistic ባለ አንድ አምላክ ናት፤» ፩ኛ ቆሮ ፰፥፬፣ ኤፌ ፬፥፫-፮፤ ፩ኛ ቆሮ ፲፪፥፮፣ ፩ኛ ቆሮ ፲፪፥፮፣ ፩ኛ ቆሮ ፰፥፮፣ ሚል ፪፥፲፣ ማር ፲፪፥፳፱። የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን «ሞኖቴይስቲክ ባለ አንድ አምላክ» ብትሆንም እንደ ብሉይ ኪዳን ትምህርት አንድ ገጽ ማለት አይደለም።እንደ አዲስ ኪዳን ትምህርት «ወእንዘ ታጠምቅዎሙ በሉ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ በምታጠምቋቸው ጊዜ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በሉ፤» ባለው አምላካዊ ትምህርት መሠረት በሶስት አካላት (በሥላሴ) በአንድ መለኰት ታምናለች።
ለ.፦ ከሐዋርያት ጀምሮ በቤተክርስቲያን ሊቃውንት ስለ አንድነትና ሦስትነት የተሰጠውን ኦርቶዶክሳዊ ምስክርነት ተቀብላ፥እነርሱ ስለ ቅድስት ሥላሴ የሰጡትን ትምህርት ታስተምራለች።ቅድስት ሥላሴ፦አብ፥ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይባላሉ።የአብ ግብሩ መውለድ፥ የወልድ ግብሩ መወለድ፥ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረጽ ነው። አብ ቢወልድ ቢያሠርጽ እንጂ እንደ ወልድ አይወለድም፥እንደ መንፈስ ቅዱስ አይሠርጽም።ወልድም ቢወለድ እንጂ እንደ አብ አይወልድም አያሠርጽም፥እንደ መንፈስ ቅዱስም አይሠርጽም።መንፈስ ቅዱስም ቢሠርጽ  እንጂ እንደ አብ አይወልድም አያሠርጽም፥እንደ ወልድ አይወለድም።ለአብ ፍጹም አካል፥ፍጹም መልክ፥ፍጹም ገጽ አለው።ለወልድም ፍጹም አካል፥ፍጹም መልክ፥ፍጹም ገጽ አለው።ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል፥ፍጹም መልክ፥ፍጹም ገጽ አለው።እነዚህ ኩነታት ይባላሉ።በዓረብኛ «ከወነ» ብሎ ቅርጽ አወጣ ይላል። ሊቃውነት ስለ ሦስትነት ባጭሩ ከዚህ በላይ እንደገለጥነው ሲያስተምሩ ለትምህርታቸው ምሳሌ ከሥነ ፍጥረት ጠቅሰዋል።
ለምሳሌ፦ ለፀሐይ ሦስትነት አለው፥ ይኸውም ሀ፦ ክበቡ፤ ለ፦ ብርሃኑ፤ ሐ፦ ሙቀቱ ነው። በክበቡ አብ፥ በብርሃኑ ወልድ፥ በሙቀቱ መንፈስ ቅዱስ ይመሰላል። ነገር ግን አንድ ፀሐይ ይባላል እንጂ ሦስት ፀሐይ እንደማይባል ሥላሴም በስም፥በአካል፥በግብር ሦስት ቢባሉም አንድ አምላክ ናቸው እንጂ ሦስት አማልክት አይባሉም።ሥላሴ በዘመነ አይቀዳደሙም፥በክብር አይበላለጡም።ሥላሴን በዘመን አቀዳድሞ፥በክብር አበላልጦ፥ ወልድ ፍጡር በመለኮቱ ያለ አርዮስ በ፫፻፳፭ ዓ.ም. በኒቂያ ጉባኤ ተረተፀቶ በሦስቱ መቶ አሥራ ስምንቱ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ተወግዟል።መንፈስ ቅዱስን ሕጹጽ ያለ መቅዶንዮስም በ፫፻፹፩ ዓ.ም. በቊስጥንጥንያ ጉባኤ ተረትቶ ተወግዟል። የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምሥጢረ ሥላሴን ሊያፋልሱ ተነሥተው የነበሩ እነዚህን መናፍቃን ስታወግዝ ትኖራለች።መንፈስ ቅዱስን ከአብና ከወልድ ሠረጸ የሚሉትንም (ካቶሊካውያንን) ታወግዛለች።
፪፦ ምሥጢረ ሥጋዌ፤ . . .
ምንጭ የኢትዮጵያ ኦርቶዲክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ
(በአባ ጎርጎርዮስ  (M.A) ፲፱፻፸፬ እና ፲፱፻፹፮ ዓ.ም.

19 comments:

 1. Ye abatachin bereket yideribin
  Kalehiwot yasemalin Amen!

  ReplyDelete
 2. Kalehiwot yasemalin Yabatachin bereket yideribin.

  ReplyDelete
 3. Kale hiwet yasemalin.
  Abatachin be "WALDIBA" kudus Gedamachin zuria TSELOT MIHILA endidereg Ebakachihu yebetekrstianua ewunetegna abatoch tenageru lemin zim tilalachihu? Zare zim binil nege BEGETE ENA BETARIK tewekashoch anihonim wey. Ke AMLAK belay manin new ferten zim yeminlew.
  AMLAKE ISRAEL ETHIOPIAN ENA HIZBUAN YITEBIKILIN

  ReplyDelete
 4. kale hiwot yasemalen
  endewe bizu yeaschewen timhert endzhie makreb bichale bebzate bewnet masebaseb binchile egzher yestlige

  ReplyDelete
 5. Kale Hiwot Yasemalin
  Regim Edme Yistilin

  ReplyDelete
 6. kalehiwet yaseman ... ye bixue abatachin bereket yederbin

  ReplyDelete
 7. kale hiwot yasemalen!

  ReplyDelete
 8. kalehiwet yasemalin ye abatachin bereket yiderbn

  ReplyDelete
 9. መናፍቃን በኢ\ኦ\ተ\ቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየፈጠሩ ያለውን ችግር ለመረዳት http://emenetsion.blogspot.com (እምነ ጽዮን) የተባለውን ጦማር ቢያነቡ ጥሩ ግንዛቤ ያገኛሉ::

  ReplyDelete
 10. በረከታቸው ይደርብን!!! በትምህርታቸው ጸንተን የመንግስቱ ወራሾች እንሆን ዘንድ የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት አይለየን!!!

  ReplyDelete
 11. መናፍቃን በኢ\ኦ\ተ\ቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየፈጠሩ ያለውን ችግር ለመረዳት http://emenetsion.blogspot.com (እምነ ጽዮን) የተባለውን ጦማር ቢያነቡ ጥሩ ግንዛቤ ያገኛሉ::

  ReplyDelete
 12. እናንተ ከእሳቸው በአካል ትምህርታቸውን ቀሰማችሁ ለኛ ማስተላለፍ ሃላፊነት እንዳለባችሁ ተረድታችሁ ይህን ለማድረግ መጀመራችሁ የሚያስመሰግን ስለሆነ በትጋትና በትራት ለመቅረብ ሞክሩ፡፡ እሳቸው የፈጠሩትን መነሳሳት እናንተ እያነደዳችሁ አቀጣጥሉት ያን ጊዜ ቤተክርስቲያናችንን የሚያገለግለው ትውልድ ይጨምራል፡፡ ለመንግስተሰማይም ብዙ ነፍሳት ይበቃሉ፡፡ ዛሬ ያጣነው በቃሉ ያለውን በግብር ገልጾ የሚያሳይ እውነተኛ መምህር ነውና በቃልም በግብርም የሚስተምሩ ተተኪዎችን ለማውጣት ጣሩልን::

  ReplyDelete
 13. ቃለሕይወት ያሰማልን ረዥም ዕድሜ ይስጥልን ያገልግሎት ዘመንዎን ያርዝምልን

  ReplyDelete
 14. ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
  ምነው ቀሲስ ፅሁፍዎት ብዙ ጊዜ አስቆጠረ፡፡ በሰላም ነው? በሰላም ከሆነ ከቆሙበት ቢቀጥሉልን ደስተኞች ነን፡፡

  ReplyDelete
 15. Kale Hiwot yasemalen. Endete new ye Abatachenen yastemaruten temeherte ena mesahfachewn magegnete yemichalew.

  ReplyDelete
 16. Kale Hiwot yasemalen! How can I get z book of "History of Ethiopian Orthodox Tewahedo Churh"???

  ReplyDelete
 17. Kesis D S,Kale hiwot yasemalin.yersachewun yewengel maid bemesatefe erasen ende edelgna ekotralehu.Kesis Yekdusan amlak egziabher beagelgloth yabertah.
  Mulugeta Assefa

  ReplyDelete