Sunday, October 2, 2011

ነገረ ማርያም ክፍል፦ ፲፮


ካለፈው የቀጠለ . . .
«ስለ ጻድቁ ስለ ዮሴፍ የምንናገረውን እንወቅ፤»
          የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ የነበረው ቅዱስ ኤራቅሊስ፦ ከቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል፥ «የበኲር ልጅዋንም እስከምትወልድ ድረስ አላወቃትም፤» የሚለውን ንባብ በተረጐመበት አንቀጽ ላይ፥ «ናእምር እንከ ዘንሔሊ በእንተ ብፁዓዊ ዮሴፍ ቅዱስ ወምእመን፥ እስመ ውእቱ ኢያእመረ ምሥጢረ ዘይትፌጸም በእግዝእትነ ቅድስት ድንግል ማርያም። የታመነ፥ የከበረ፥ የተመሰገነ ስለሚሆን ስለዮሴፍ የምንናገረውን እንወቅ፥ እርሱ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም የሚፈጸመውን ምሥጢር አላወቀምና፤» ብሏል። ይኸውም፦ ትምህርታቸው በሊቃውንት ደረጃ የሁኑ፥ ነገር ግን ቃሉን ያለ መንገዱ የሚተረጉሙ መናፍቃን በመነሣታቸው ለእነርሱ መልስ ይሆን ዘንድ ነው። «የምንናገረውን እንወቅ፤» ማለቱም «እናስተውል፤» ማለቱ ነው። ምክንያቱም ምን ቢማሩ ባለማስተዋል መጥፋት፥ ማጥፋትም አለና ነው። ሊቃውንት ዕውቀታቸውን በትህትና ካልያዙትና በጸሎት ካልጠበቁት በስተቀር መሰናክል እንደሚሆንባቸው ከጥንት ጀምሮ ከተነሡ መናፍቃን መረዳት ይቻላል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በግሉ በጸሎት ከመትጋት ጋር ምእመናንን፦ «በምስጋና እየተጋችሁ ለጸሎት ፅሙዳን ሁኑ። ስለ እርሱ የታሰርሁለትን የእግዚአብሔርን ምሥጢር እንድንናገር፥ እግዚአብሔር የቃሉን በር ይከፍትልን ዘንድ ለእኛም ደግሞ ጸልዩልን፤ ለምኑልንም፤ ልናገርም እንደሚገባኝ እገልጠው ዘንድ ጸልዩልኝ፤» ይል የነበረው በአገልግሎቱ  ችግር እንዳይፈጠር ነበር። ቈላ ፬፥፪-፬። በመሆኑም ሐዋርያውን አብነት አድርጎ፥ በጸሎት የተጋ፥ በትህትና ያጌጠ፥ በደጋግ ምእመናን ጸሎት የተጠበቀ ቅዱስ ኤራቅሊስ «አላወቃትም፤» የሚለውን እንደሚከተለው ተርጉሞ አስተምሯል።
ሀ፦ ጻድቁ ዮሴፍ አገልጋይ የሆነለትን ምሥጢር (በተዋሕዶ አምላክ ሰው፥ ሰውም አምላክ የሆነበትን ምሥጢር) አላወቀም፤ ለእርሱ ከታጨችለት (እንዲጠብቃት፥ እንዲያገለግላት ከተሰጠችው) ከድንግል፥ ነቢያት ስለ እርሱ፦ «ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ (ከሥጋ መቅሠፍት የምትድኑበትን ምልክት ስላመናችሁ ከነፍስ መቅሠፍት የምትድኑበት ምልክት ይሰጣችኋል)፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም (ወልድን) ትወልዳለች፤ (ምልክት ያልኳችሁም ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለዷን ነው)፤ ስሙንም አማኑኤል (አምላክ ወሰብእ፥  እግዚእ ወገብር) ትለዋለች። . . .  ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም (ወልድ) ተሰጥቶናልና፤ (ለሕማም፥ ለሞት ተሰጠልን)፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ (ለጌታ ሥልጣን የባሕርዩ ነው፤ አንድም መስቀል በትከሻው ላይ ነው፤ አንድም የደከመን ሰው በትከሻ ተሸክመው እንዲያሳርፉት፥ እርሱም በሚቀበለው መከራ ነፍሳትን ያሳርፋል)፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፤» በማለት የተናገሩለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ያለ ዘር አንዲወ ለድ አላወቀም፤ (ሕፃን ያለ አባት እንዲገኝ አላወቀም)። ኢሳ ፯፥፲፬፣ ፱፥፮-፯። ይኽንን ታላቅ ምሥጢር የተረዳ ፊለጶስ ግን፦ «ሙሴ በኦሪት ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉለትን የናዝሬቱን ኢየሱስን አገኘነው፤» ብሏል። እንዲህ የተባለ ናትናኤል፥ ለጊዜው ምሳሌ ኦሪትና ትንቢተ ነቢያት የተፈጸመበትን ምሥጢር ባለማወቁ፦ «በውኑ ከናዝሬት ደግ ሰው ሊወጣ ይችላልን?» ሲል ጠይቋል። ለፍጻሜው ግን፥ ምሥጢሩን በማወቁና በመረዳቱ መምህር ሆይ፥ በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ የእስራኤልም ንጉሥ አንተ ነህ፤» በማለት እምነቱን መስክሯል። ጌታም፦ «በበለስ ዛፍ ሥር አየሁህ፤ (ሄሮድስ ሕፃናትን ባስፈጀ ጊዜ፥ ወላጆችህ በንብ ቀፎ አድርገው ከበለስ በታች ሲደብቁህ የጠበኩህ እኔ ነኝ፤ ወጣት ሳለህም ከበለስ በታች ከሰው ተሰውረህ ያፈሰስከውን ደም፥ ያሳለፍከውን ነፍስ (የበደለህን ሰው እንደገደልከው) እኔ አውቃለሁ)፤ ስላልኩህ አመንህን? ገና ከዚህ የሚበልጥ ታያለህ፤» ብሎታል። ዮሐ ፩፥፵፬-፶፩።
ለ፦ ጻድቁ ዮሴፍ፦ ነቢዩ ኢሳይያስ፥ «የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን (መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያልወ ደቀባትን ዘር ድንግል ማርያምን) ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንን፥ እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር። (ዕድል ፈንታችን ጽዋ ተርታችን በማይጠፋ እሳት መቃጠል ይሆን ነበር)።» እንዳለ፥ ከንጹሕ ዘር የተፈጠረች ድንግል የእግዚአብሔር ማደሪያ እንድትሆን፦ (እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ፤ ተብሎ በቅዱስ ዳዊት አንደበት በእግዚአብሔር የተነገረላት እርሷ መሆኗን) አላወቀም። ኢሳ ፩፥፱ ፣ መዝ ፩፻፴፩፥፲፫። ዳግመኛም፦ በጻድቁ በኖኅ አንደበት፥ «እግዚአብሔር . . . በሴም ድንኳን ይደር፤» የተባለላት (የሴም ድንኳን ምሳሌዋ የሆነላት) እርሷ መሆኗን አላወቀም። ዘፍ ፱፥፳፯። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ «ሁለተኛው አዳም ግን ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤» ብሎ እንደተናገረለት ዳግማይ አዳም ክርስቶስ ድንግ ልና ካላት ገነት (ጠቢቡ ሰሎሞን እኅቴ ሙሽሪት የተቈለፈች ገነት፥ የተዘጋች ገነት፥ የታተመችም ጉድጓድ ናት ብሎ ከተናገረላት እመቤት) እንዲገኝ አላወቀም። ፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፵፭፣ መኃ ፬፥፲፪።
ሐ፦ ጻድቁ ዮሴፍ፦ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ፦ «ሁሉም በእርሱ ሆነ፤ ከሆነውም ያለእርሱ ምንም የሆነ የለም፤» ብሎ የመሰከረለት፥ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም፦ «ይኸውም የማይታይ እግዚአብሔርን የሚመስለው (በባሕርይ የሚተካ ከለው)፥ ከፍጥረቱ ሁሉ በላይ የሆነ በኲር ነው። (የፈጠረውን ፍጥረት የሚገዛ የፍጥረታት አለቃ ነው)። በእርሱ ቃልነት እግዚአብሔር ሁሉን ፈጥሮአልና፥ በሰማይ ያለውን በምድርም ያለውን፥ የሚታየውንና የማይታየውን፥ መናብርትም ቢሆኑ፥ አጋእዝትም ቢሆኑ፥ መኳንንትም ቢሆኑ፥ ቀደምትም ቢሆኑ፥ ሁሉን በእርሱ ቃልነት ፈጥሮአቸዋልና፤ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ ተፈጠረ፤ እርሱ ከሁሉ አስቀድሞ ነበረ፤ ሁሉም በእርሱ ጸና።» በማለት የተናገረለት፥ ፍጡራንን ሁሉ የፈጠረ ክርስቶስ ያለዘር እንዲወለድ አላወቀም። ዮሐ ፩፥፬፣ ቈላ ፩፥፲፭-፲፰። ዳግመኛም ጠቢቡ ሰሎሞን፥ «አበባ በምድር ላይ ታየ፤ (አበባ ክርስቶስ ከምድር ከተፈጠርን ከእኛ በሥጋ ተገለጠ)፤» ብሎ እንደተናገረ፥ ነቢዩ ዳዊትም፦ «ምድርም ፍሬዋን ትሰጣለች (ከእኛ ከምድራዊያን ወገን ከሆነች ከድንግል ፍሬ ክርስቶስ ይወለዳል)፤» በማለት እንደተነበየ፥ «እነሆ፥ ጻድቅ ንጉሥ ይነግሣል፤ (ጻድቅ ንጉሥ ጌታ በማኅፀነ ድንግል ይነግሣል፥ አንድም በማዕከለ ሐዋርያት ይነግሣል፥ አንድም በመስቀል ላይ ይነግሣል)፤ መሳፍንትም በፍርድ ይገዛሉ። (ቅዱሳን ሐዋርያት በእውነት ያስተምራሉ)።» እንዳለ፥ ይህ ሁሉ የተነገረለት አምላክ ከእርሷ እንዲወለድ አላወቀም። መኃ ፪፧፲፪፣ መዝ ፹፭፥፲፪፣ ኢሳ ፴፪፥፩።
ትንቢተ ነቢያት የሚፈጸምበት ዘመን ሲደርስ፥የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል፥ ከእግዚአብሔር ተልኮ በመምጣት፥ «ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነት አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅንም (ወልድን) ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ። . . . መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፤ የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል፤» አላት። ሉቃ ፩፥፳፮-፴፭። የድንግል ሆዷ ገፋ፥ ያለዘር የፀነሰች የድንግል የሆዷን መግፋት ባየ ጊዜ፥ የዮሴፍ ልቡ አዘነ፤ የንጽሕት እመቤታችንን ምሥጢሯን ፈጽሞ መረመረና በማያውቀው ምሥጢር ፀንሳ ቢያገኛት በጽኑ አሳብ በማውጣት በማውረድ ተያዘ፥ ፀንሳ አገኛት፥ በዘር የፀነሰችም መሰለው፤ ከእግዚአብሔር የተላከ መልአክ «የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርሷ የሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ ነውና፤» ብሎ እስኪነግረው ድረስ ተቸግሮ ነበር። ማቴ ፩፥፳። ዮሴፍም ይህን በሰማ ጊዜ ለድንግል ሰገደ፥ ንጽሕናዋንም አመነ፤ ነቢዩ ኢሳይያስ፦ «እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙም አማኑኤል ይባላል፥ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ባሕርይ ጋር አንድ ሆነ ማለት ነው፤» ብሎ የተናገረላት ድንግል እርሷ እንደሆነች አወቀ። 

15 comments:

 1. አባታችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
  ፀጋውን ያብዛሎት።

  ReplyDelete
 2. KHY mengeste semayaten yawurselen amen

  ReplyDelete
 3. What can i say weladite amlak abzeta tebarko

  ReplyDelete
 4. kale hiwoten yasemalen melake selam.

  ReplyDelete
 5. kale hiwet yasemalen
  yemechale kewone teketataye temertu be demese behone

  ReplyDelete
 6. አባታችን ጊታ እኛን ልጆችወትን የማስተማርያ ዘላቂይ አቅምና ሀይል እንዲሰጥወት የዘወትር ጸሎቲ ነወ።
  ከምስጋናየ ባሻገር ግን በእግዚአብሒር እርዳታ ሙሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የምናካሂድበት አንድ ድህረ ገጽ
  ቢያዘጋጁልን ለብዙ የኣርተዶክስ ልጆችወት በቀላሉ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የሚያመች ይመስለኛል።
  Good Amharic Books የተባለ ድህረ ገጽ የኛ መስሎኝ ማንበብ ከጀመርኩ በሃላ የጸረ ድንግል ማርያም እና ቅዱሳን አባቶች
  መሆኑንን ሳውቅ አቆመኩ። ከዛ በመነሳትም ነው ይህንን ጥያቂ ለማንሳት የተገደዱኩት። በዚህ አጋጣሚ ለምእመናን ልጦቅም የምፈልገው እንደኒ መግቢያውን ሳታነቡ ሽፉንን ብቻ በመመልከት ምንም አይነት ቅዱሳት መጽሐፍ እንዳታነቡ ነው።

  አጽባእተ ድንግል

  ReplyDelete
 7. Ene Bezihe ers lemetaf feligie sayihon Aba minew beselem new yetefut lematet new

  ReplyDelete
 8. EMABATACHEN ATELAYANE KALA HEIWOT YASAMALEN

  ReplyDelete
 9. Abatachin, kale hywet yasemalin. be'edme betsega yitebklin.

  ReplyDelete
 10. kale hiwot yasemalin ;riste mengste semay yawrslin

  ReplyDelete
 11. abatachin kale hiwotin yasemalin amen. tsegawon yabzaliwo be edme yakoyilin amen.

  ReplyDelete
 12. KALE HIWOT YASEMALEN YEMEBETACHEN FIKER YEDEREBEN

  ReplyDelete
 13. egzeabher amalk yeagelgilot edmewoon yibarkilin,bebetu akoyitoo tsegawun yabzalin bertu tenkiruu lijoochuwootin kemastemar kememker wedehuwala ayibelu.tnx egnanim betseloto asibun(gbre eyesus negn)

  ReplyDelete