Tuesday, May 31, 2011

ክ.፪ «እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤» ማቴ ፲፥፲፮፤


ክፍል ፪
፩፥፮፦ «ምንም አትያዙ፤»
               
          ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦ ደቀመዛሙርቱ ለስብከተ ወንጌል በሚሠማሩበት ጊዜ ምንም መያዝ እንደሌለባቸው ሲነግራቸው፦ «ወርቅ ወይም ብር ወይም ናስ በመቀነታችሁ ወይም እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና፤» ብሏቸዋል። ምክንያቱም፦ የተሰጣቸው ጸጋ ከዚህ ሁሉ በላይ በመሆኑ ነው። እነዚህ ያልቃሉ፥ የተሰጣቸው ጸጋ ግን ፈጽሞ አያልቅም። እነዚህን ማለትም የሚ ያልፉትንና የሚጠፉትን ይዘው ከተጓዙ የእግዚአብሔርን ቸርነት ስለሚሸፍንባቸው የምንገዛበት ወርቁን ብሩን ባን ይዝ ኖሮ ረሀቡ በገደለን ነበር፤ መለወጫ ልብስ ባንይዝ ኖሮ ልብሳችን አልቆ ብርዱ በገደለን ነበር፤ ጫማ ባንይዝ ኖሮ እንቅፋቱ፥ እሾኹ በጐዳን ነበር፤ በትር ባንይዝ ኖሮ አራዊቱን፥ ዕባቡን፥ ጊንጡን በምን እንከላከል ነበር፤ ማለ ታቸው አይቀርምና ነው።
                                                                        
          ጌታችን ደቀመዛሙርቱን «ምንም አትያዙ፤» ያላቸው፥ አገልግሎቱን የሚፈጽሙት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በመሆኑ ነው። ትንሣኤውን በገለጠላቸው ጊዜ፦ «እናንተ ግን ከአርያም ኀይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ተቀመጡ።» ያላቸው ለዚህ ነበር። ሉቃ ፳፬፥፵፱። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ፦ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ሆነው በቤተ መቅደስ ደጅ ያገኙትን እግረ በሽተኛ፦ «ወርቅና ብር የለኝም፤ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ፥ በናዝሬቱ  በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥተህ ሂድ አለው። በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ ያንጊዜም እግሩና ቊርጭምጭሚቱ ጸና። ዘሎም ቆመ፤ እየሮጠና እየተራመደም ሄደ፤ እግዚአብሔርንም እያመስገነ ከእነርሱ ጋር ወደ ቤተ መቅደስ ገባ።» የሐዋ ፫፥፩-፰።

          ቅዱስ ዳዊት፦ ሁሉ በእጁ፥ ሁሉ በደጁ የሆነ ንጉሥ ቢሆንም በወርቅና በብር አልተመካም። በመሆኑም፦ «ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል፤» ብሏል። መዝ ፻፲፰፥፸፪። ምክንያቱም ፍቅረ ንዋይ ልቡ ናን ለሁለት ስለሚከፍል ነው። ገንዘብ በዚህ ዓለም አምላክ ሆኖ ሁሉን ስለገዛ ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንቅፋት ሆኗል። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦ «እንግዲህ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትች ሉም፤» ያለው ለዚህ ነው። ማቴ ፮፥፳፬። በሉቃስ ወንጌልም ላይ፦ «ዕወቁ፤ ከቅሚያም ሁሉ ተጠበቁ፤ ሰው የሚድ ን ገንዘብ በማብዛት አይደለምና፤» ብሏል። ሉቃ ፲፪፥፲፭። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም፦ «ምግባችንን እና ልብሳች ንን ካገኘን ይበቃናል። ባለጸጋ ሊሆኑ የሚወዱ ግን በጥፋትና በመፍረስ፥ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ፥ በሚጎ ዳም በብዙ ምኞትና በፈተና፥ በወጥመድም ይወድቃሉ። ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ ይህንን በመ መኘት ተሳስተው ሃይማኖታቸውን የለወጡ ብዙዎች ናቸውና፥ ለራሳቸውም ብዙ መቅሠፍትን ሽተዋልና።» ብሏል። ፩ኛ ጢሞ ፮፥፰። በብሉይ ኪዳን እንኳ እነ ነቢዩ ኤላሳዕ የእግዚአብሔር ጥሪ ሲደርሳቸው፥ ከቤታቸው የወ ጡት ባዶ እጃቸውን ነው።

          ለመምህራን ወርቃቸው፥ ብራቸው፥ ናሳቸው፥ ልብሳቸው፥ ምርኲዛቸው የሚያስተምሯቸው (እረኛ ሆነው የሚጠብቋቸው) ምእመናን ናቸው። ይኽንንም በተመለከተ፥ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ «ከቶ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው? ወይስ ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? (ወይን ተክሎ አርሞ ኰት ኲቶ ከአዕዋፍ ጠብቆ የማይመገብ ማን ነው?) ወይስ መንጋ እየጠበቀ ከመንጋው ወተት የማይጠጣ ማን ነው? (መንጋውንስ ከአራዊት ጠብቆ፥ ለምለም ሣር ጥሩ ውኃ መግቦ፥ ወተቱን የማይጠጣ ማን ነው? ልክ እንደዚህ እኛም አስተምረን፥ አሳምነን፥ አጥምቀን፥ አቊርበን፥ ከአጋንንት ጠብቀን፥ ለቁመተ ሥጋ ያህል የዕለት እራት መመገ ብ አይገባንምን?) በውኑ ለሰው ይምሰል እናገራለሁን? የሙሴ መጽሐፍ ኦሪትስ፦ እህልህን በምታበራይበት ጊዜ የበሬውን አፉን አትሰረው። ብሎ የለምን? እንግዲህ ይህን የጻፈ ለእግዚአብሔር በሬ አሳዝኖት ነውን? ይህን የሚለው ፈጽሞ ስለ እኛ አይደለምን? የሚያርስ በተስፋ ሊያርስ፥ የሚያበራይም እንዲካፈል፥ በተስፋ ሊያበራይ ስለሚገባው በእውነት ስለእኛ ተጽፏል። እኛ መንፈሳዊውን ነገር ከዘራንላችሁ ሥጋዊውን ነገር ብናጭድ ታላቅ ነገር ነውን? (ተራራ ያህል አስተምረናችሁ ድምብላል ያህል ብንመገብ ቁም ነገር ነውን? ሌሎች (ሐሰተኞች አንኳ) በእናንተ ላይ ይህን መብት የሚካፈሉ ከሆኑ እኛማ (እኛ እውነተኞቹ) ይልቁን እንዴታ? (በእኛ ሹመት ሌላ የሚቀ ድመን ማለትም ተመሳስለው የገቡ ሐሰተኞች ወንጌላውያን የሚጠቀሙ ከሆነ፦ የሚሻላችሁን እናንተ ታውቃ ላችሁ)፤ እኔ ይህን አልፈለግሁትም፤ ነገር ግን የክርስቶስን ትምህርት እንዳላሰናክል በሁሉ እታገሣለሁ። (እንዲህ ም ሳሌ የሚያስመስልህ፥ ኦሪት የሚያስጠቅስህ ሽተኸው (ፈልገኸው) ነውን? ትለኝ እንደሆነ፥ እኔስ ይህን ሽቸው አይደ ለም፤ ደሀው በማጣት፥ ባዕለጸጋው በንፍገት የክርስቶስን ትምህርት ወንጌልን እንዳላስቀር በውስጥ በአፍአ እታገ ሣለሁ)። የጣዖታቱ ካህናት የጣዖታቱን መባ እንደሚበሉ አታውቁምን? መሠዊያውን የሚያገለግሉም መሥዋዕቱን እንደሚካፈሉ አታውቁምን? ለቤተ እግዚአብሔር ሹሞች መተዳደሪያቸው የቤተ እግዚአብሔር መባ ነው። ጌታች ንም እንዲሁ ወንጌልን ለሚያስተምሩ ሰዎች ለሕይወታቸው መተዳደሪያ በዚያው ወንጌልን በማስተማር ይሆን ዘን ድ አዘዘ።(ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጓል።)» ብሏል። ፩ኛ ቆሮ ፱፥፮-፲፬።

፩፥፯፦ በጥንቃቄ መርምሩ፤

          ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦ ምንም መያዝ እንደሌለባቸው ከነገራቸው በኋላ፦ «በምትገቡባትም በማናቸይቱም ከተማ ወይም መንደር በዚያ የሚገባው ማን እንደሆነ በጥንቃቄ መርምሩ። (ደግ ሰው የበቃ ሰው ማን አለ? ብላችሁ ጠይቁ)። ለማስተማር እስክትወጡ ድረስ ከዚያ ተቀመጡ። (በዓታችሁን አጽኑ ፥ ምእመናን ለመማር በመጡ ጊዜ እንዳያጧችሁ ተጠንቀቁ)። ብሏቸዋል። ምክንያቱም መንፈሳውያን የሚመስሉ ሥጋውያን፥ ቀናዎች የሚመስሉ ብዙ ጠማሞች ስላሉ ነው። የሚበዛውም ወረተኛ በመሆኑ ነው። ይህች ዓለም ለጽ ድቅ ሳይሆን ለዝና ጌታን ምሳ እንደጋበዘው ፈሪሳዊ ዓይነት ሰዎች የሚበዙባት ስለሆነ በተሰጣቸው መንፈሳዊ ጸጋ እንዲመረምሩ ነው። መንፈሳዊ ሰው (መንፈስ ቅዱስ ያደረበት) ሁሉን ይመረምራልና። ፩ኛ ቆሮ ፪፥፲፭።

          ይህ የጌታ መመሪያ ቋሚ ሕግ ነው። በመሆኑም መምህራን ልንከተለው ይገባል። የሥጋችንን ምቾት ለመ ጠበቅ ካገኘንበት ዘው የምንል ከሆነ በብዙኃኑ ዘንድ ተቀባይነትን እናጣለን። ፍጹም መንፈሳዊ ከሆነ ደሀ ይልቅ፥ ፍጹም ሥጋዊ የሆነ ሀብታምን የምንመርጥ ሰዎች፥ ወንጌልን ለመስበክ በዐውደ ምሕረቱ ላይ ስንቆም የሚታዘበን ይበዛል። እየመሰለን ነው እንጂ የሚያከብሩን ድሆቹ ናቸው፥ ሀብታሞቹማ በገንዘባቸው እንደገዙን ሸቀጥ ነው የሚ ቆጥሩን፤ እነዚህ ሰዎች መምህራኖቹን በራሳቸው አሳብ ሲመሯቸው ይስተዋላል። የተጠማው ሕዝብ ምነው ትምህ ርቱ ባላለቀብን የሚለውን እነርሱ «ሕዝቡ ብዙ ጉዳይ ስላለው ትምህርቱ አጠር ይበል፥ ቅዳሴው አጠር ይበል፥ በእኛ ቤተክርስቲያን ጾም ይበዛል፥ በአንድ እርፈ መስቀል መቁረብ ለበሽታ ሊያጋልጥ ይችላል፥» ወዘተ--- የሚለ ውን አሳብ እያቀረቡ መምህራኑን ይሸረሽሯቸዋል ወይም በይሉኝታ ባለመኑበት መንገድ ይመሯቸዋል። በተለይም ከቦታ ቦታ የምንንቀሳቀስ መምህራን የት ማረፍ እንዳለብን ከመንፈሳዊነት አንፃር መምረጥ አለብን። መንፈሳውያን ሰዎችን በማስተናገድ የሚታወቁ ብዙ ዓመፀኞች አሉና። እኛም ሁለት ቀን ስላስተናገዱን ብቻ በየሄድንበት «እገሌ ቅዱስ ነው፥ እገሊት ቅድስት ናት፤» እያልን የምንሰብክላቸው አስመሳዮች ብዙዎች ናቸውና። በሞቴ ብለው አብል  ተው አጠጥተው መልሰው በሐሜት ሰውን የሚበሉ፥ እንደፍላጐታቸው ካልሆንላቸው ስም የሚያጠፉ እነዚህ ናቸ ው። ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ፦ «እናንተ ግን ድሆችን አቃለላችኋቸው፤ የሚቀሙአችሁ፥ ወደ ሙግትና ወደ ሸንጎ ም የሚጐትቷችሁ፥ እነዚያ ባለጠጎች አይደሉምን?» ያለው ለዚህ ነው ያዕ ፩፥፮። ከሁሉም በላይ ጌታ ራሱ በወንጌ ል፦ «እውነት እላችኋለሁ ባለጸጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባ ዘንድ ጭንቅ ነው። ዳግመኛም እላችኋለሁ፦ ባለጸጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል፤» ብሏል። ማቴ ፲፱፥፳፫። እኛን ደግሞ (ከታች እስከ ላይ ያለነውን አገልጋዮች) የሚያንጠለጥልን ሀብታም ላይ ነው፤ ይህም ነፍስ ለማዳን ሳይሆን ተጠግተን ለመጠቀም ብቻ ነው። እንዲህም ሲባል በሚበዛው ለመናገር እንጂ ከሀብታም ተጠግ ተው፥ አስተምረው፥ መክረው፥ ገሥጸው፥ ለንስሐ ለሥጋ ወደሙ ያበቁ የሉም፥ ለማለት አይደለም። ከሀብታሞቹም ሀብት የሰጣቸውን ፈጣሪ ያልረሱ፥ አድባራትን፤ ገዳማትን የሚረዱ፥ ነዳያንን የሚጐበኙ አሉ። ስለዚህ፦ «በጥንቃቄ መርምሩ፤» እንደተባለ መመርመር ያስፈልጋል።

          ከምዕመናን እየተጠቀምን እነርሱን የማንጠቅማቸው (የማናድናቸው) ከሆነ የመንጋው ጌታ እግዚአብሔር ይጠይቀናል። «ወተቱን ትጠጣላችሁ፤ ጠጉሩንም ትለብሳላችሁ፤ የወፈሩትን ታርዳላችሁ። በጎቹን ግን አታሰማ ሩም፤ የደከመውንም አላዳናችሁትም፤ የታመመውንም አልፈወሳችሁትም፤ የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም፤ የባዘ ነውንም አልመለሳችሁትም፤ የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም፤ በኀይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው። በጎቼም እረኛን በማጣት ተበተኑ፤ ለዱር አራዊትም ሁሉ (ለመናፍቃን) መብል ሆኑ።» ይለናል። ሕዝ ፴፬፥፫

፩፥፰፦ ሰላምታ ስጡአቸው፤

          የመምህራን ሥራ ሰላም ላጣው ዓለም ሰላምን መስጠት ነው፤ ለዚህም ነው፥ ጌታችን፦ «ወደ ቤትም በገ ባችሁ ጊዜ፥ ሰላምታ ስጡአቸው። (እጅ ንሷቸው፥ አክብሯቸው እንጂ አክብሩን አትበሉ)።» ያላቸው። በመቀጠ ልም፦ «ለዚያ ቤት የሚገባው ቢሆን ሰላማችሁ ይደርበት የማይገባው ቢሆን ግን ሰላማችሁ ወደ እናንተ ይመለስ። (የበቃ ደግ ሰው ከተገኘ ሰላማችሁ እኔ ክርስቶስ ሰውነቱን ማደሪያ አደርገዋለሁ፥ የበቃ ደግ ሰው ካልተገኘ ግን ሰላማችሁ እኔ ክርስቶስ በእናንተ እንዳደርኩ እቀራለሁ)።»  ብሏቸዋል።

          የሰላም ባለቤት ሰላማዊ ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ነቢዩ ኢሳይያስ፦ «ፍትሕን የሚጠብቅና ጽድቅን የሚያደርግ ሕዝብ ይገባ ዘንድ በሮችን ክፈቱ። በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ የምትደገፍ ነፍስን በሰላም ትጠብ ቃታለህ።» ያለው እርሱን ነው። ኢሳ፳፮፥፪። በተወለደ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት፦ «ሰላም በምድር፤» እያሉ የዘመሩት ለዚህ ነበር። ሉቃ፪፥፲፬። በትምህርቱም፦ «ሰላምን እተውላችኋላሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው አይደለም፤» ብሏል። ዮሐ፲፬፥፳፯። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፥ ጌታ፦ ይህን ሰላም እንዴት እንደሰጠን ሲናገር፦ «ሁሉንም በእርሱ ይቅር ይለው ዘንድ በመስቀሉ ባፈሰሰው ደም በምድርና በሰማያት ላሉ ሰላምን አደረገ፤» ብሏል። ቈላ ፩፥፳። በኤፌሶን መልእክቱም፦ «አሁን ግን ቀድሞ ርቃችሁ የነበራችሁ እናንተ በኢ የሱስ ክርስቶስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀረባችሁ። ሁለቱን (ሕዝብና አሕዛብን) አንድ ያደረገ ሰላማችን እርሱ ነው ና፥ በሥጋውም በመካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ ጥልን ሻረ። ሁለቱንም አድሶ አንድ ያደርጋቸው ዘንድ በሥርዐቱ የትእዛዝን ሕግ አጠፋ፤ እርቅንም አደረገ። በመስቀሉም በአንድ ሥጋው ሁለቱን ወደ እግዚአብሔር (ወደ ባሕርይ  አባቱ፥ ወደ ራሱና፥ ወደ ባሕርይ ሕይወቱ ወደ መንፈስ ቅዱስ) አቀረባቸው፤ በእርሱም ጥልን አጠፋ። መ ጥቶም ቀርበን ለነበርነው ሰላምን፥ ርቃችሁ ለነበራችሁት ለእናንተም ሰላምን ሰጠ።» ብሏል። ኤፌ ፪፥፲፫። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው በኋላ፦ ከአንዴም ሁለት ጊዜ በዝግ ቤት እየገባ ደቀመ ዛሙቱን፦ «ሰላም ለእናንተ ይሁን፤» ያላቸው ለዚህ ነው። ዮሐ ፳፥፲፱-፳፮።

          የበላይ ለበታች፥ የበታች ለበላይ፤ ወላጅ ለልጆች፥ ልጆች ለወላጅ፤ ወንድም ለወንድሙ፤ ባል ለሚስቱ፥ ሚስት ለባሏ፤ መምህር ለደቀመዝሙር፥ ደቀመዝሙር ለመምህር፣ በአጠቃላይ ማንም ለማንም ሰላም በማይ ሰጥበት ዓለም የሰላም ሰው ለመሆን እንደ ሻማ መቅለጥን ይጠይቃል። ጌታችን ለዓለም ሰላምን ሰጥቷል፥ ዓለም ግን ለእርሱ ሰላምን አልሰጠውም፥ ገርፎ ሰቅሎታል። ደቀመዛሙርቱም የሰላምን ወንጌል ሰብከዋል፥ ለእነርሱም ዓለም ሰላምን አልሰጣቸውም፥ በሰይፍ መትሮ፥ በመጋዝ ተርትሮ በእሳት አቃጥሎ ገድሏቸዋል። እነርሱን በተመ ለከተ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ «የገረፉአቸው፥ የዘበቱባቸውና ያሠሩአቸው፥ ወደ ወኅኒ ያገቡአቸውም አሉ። በ መጋዝ የሰነጠቁአቸው፥ በድንጋይ የወገሩአቸው፥ በሰይፍም ስለት የገደሉአቸው አሉ፤ ማቅ፥ ምንጣፍና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ተጨነቁ፤ ተቸገሩ፤ መከራ ተቀበሉ፤ ተራቡ፥ ተጠሙም። ዓለም የማይገባቸው እነዚህ ናቸው፤ ዱር ለዱርና ተራራ ለተራራ፥ ዋሻ ለዋሻና ፍርኩታ ለፍርኩታም ዞሩ፤» ብሏል። ዕብ ፲፩፥፴፮-፴፰። ይኽንንም፦ «ዓለም ቢጠላችሁ አስቀድሞ እኔን እንደጠላ ዕወቁ። እናንተስ ከዓለም ብትሆኑ ዓለም በወደዳችሁ ነበር፤ ዓለም ወገኖቹን ይወዳልና፤» ነገር ግን እኔ፦ ከጌታው የሚበልጥ አገልጋይ የለም ያልኋችሁን ቃሌን አስቡ፤ እኔን ካሳደዱ እናንተንም ያሳድዱአችኋል፤» በማለት አስቀድሞ ጌታችን ተናግሮታል። ዮሐ ፲፭፥፲፰-፳። በመሆኑም የዓለም ምላሽ በተቃራኒ ው ቢሆንም ለዓለም ሰላም መስጠት ከእኛ ይጠበቃል።

፩፥፱፦ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ፤

          ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን፦ «ከማይቀበላችሁ ቃላችሁንም ከማይሰማችሁ ግን ከዚያች ቤት፥ ወይም ከዚያች ከተማ ወጥታችሁ፥ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ። ከዚያች ሀገር ይልቅ በፍርድ ቀን ሰዶምና ገሞራ ዕረፍት እንደሚያገኙ እውነት እነግራችኋለሁ።» ብሏቸዋል። ይኸውም፦ እንኳን ገንዘባችሁ፥ ትቢያችሁ አልተከተለንም፤ ይህ ትቢያ ከእግራችን እንደረገፈ በሥጋችሁ በመቅሠፍት ትረግፋላችሁ፥ በነፍሳችሁ ደግሞ በገሃነም እሳት ትጠፋላችሁ ለማለት ነው። ምክንያቱም ቅዱሳንን መቀበል እርሱን መቀበል ነውና፤ እነርሱን አለመቀበልም እርሱን አለመቀበል ነውና፤ እርሱ ራሱ፦ «እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔ ንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።» ብሏል። ማቴ ፲፥፵።

2 comments:

  1. ቃለ ህይወት ያሰማልን አባታችን። ስብሀት ለእግዚአብሔር ልዑል ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።

    ReplyDelete
  2. yasemie leke kale hiywet!

    ReplyDelete